የአሜሪካ መልዕክት ለኢራንአሜሪካ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ተጨዋቾች ለመቀበል ችግር እንደሌለባት…

- Advertisement -
Sidebar AD
የአሜሪካ መልዕክት ለኢራን
አሜሪካ ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ተጨዋቾች ለመቀበል ችግር እንደሌለባት ገለፀች።
የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ሀገራቸው የኢራን ብሔራዊ ቡድን በአለም ዋንጫው እንዳይሳተፍ አልከለከለችም ሲሉ ተናግረዋል።
የውጪ ጉዳይ ሚንስትሩ ዋሽንግተን ኢራናዊያን ተጨዋቾች በ 2026ቱ የዓለም ዋንጫ መሳተፋቸው ላይ ተቃውሞ እንደሌላት ገልፀው ነገር ግን ከኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጥበቃ ዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸው አካላት በውድድሩ የመሳተፍ እድል እንደሌላቸው ገልፀዋል።
በፈረንጆቹ የካቲት 28 በአሜሪካ እና እስራኤል የጋራ ጥቃት የተከፈተባት ኢራን በዓለም ዋንጫው የመሳተፍ እድሏ አጠራጣሪ ሆኖ የቆየ ሲሆን በተለይም ሀገሪቱ ጨዋታዎቿን በአሜሪካ ለማድረግ ዝግጁ አይደለችም ተብሏል።
የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማርክ ሩቢዮ ወደ አሜሪካ አትምጡ ያላቸው የለም ሲሉ ገልፀው የኛ ችግር ተጨዋቾቹ ሳይሆን ከአብዮታዊ ዘቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው የብሄራዊ ቡድኑ አካላት ናቸው ብለዋል።
ሩቢዮ አክለውም የአብዮታዊ ዘቡ አሸባሪዎችን ወደ ሀገራችን በማምጣት ጋዜጠኞችና አሠልጣኞች እንደሆኑ ማስመሰል አይችሉም በማለት ተናግረዋል።
ከሩቢዮ ጎን የነበሩት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደራቸው ተጨዋቾቹ ላይ ተፅዕኖ ማሳደር እንደማይፈልግ ገልፀዋል።
የኢራንን የአለም ዋንጫ ተሳትፎ በተመለከተ ይፋ የሆነ ነገር ባይኖርም ከትናንት በስቲያ የመንግስት ቃል-አቀባይ የሆኑት ፋቴሜህ ሞሃጀራኒ ለውድድሩ አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉበወጣቶች እና ስፖርት ሚኒስቴር በኩል መደረጋቸውን አረጋግጠዋል።
የዓለም ዋንጫው በፈረንጆቹ ሰኔ 11 ሲጀምር ኢራን ከቤልጂየም ፣ ግብፅ እና ኒውዚላንድ ጋር መደልደሏ ይታወሳል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: