የኢራን ዩራኒየም እና የሰላም ድርድሩ አዲስ ማነቆ!የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን የዩራኒየም ክምችቷን አሳልፋ ለ…

- Advertisement -
Sidebar AD
የኢራን ዩራኒየም እና የሰላም ድርድሩ አዲስ ማነቆ!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “ኢራን የዩራኒየም ክምችቷን አሳልፋ ለመስጠት ተስማምታለች” በማለት ቢናገሩም ኢራን ግን “ፈጽሞ የማይታሰብ ነው” በማለት ውሳኔዋን አስታውቃለች።
ዩራኒየም ከመሬት የሚወጣ ማዕድን ቢሆንም ግን እንደወጣ በቀጥታ ጥቅም ላይ አይውልም። ጠቃሚው ክፍል እንዲበዛ የማድረግ ሂደት “ማበልጸግ” ይባላል። ዝቅተኛ ደረጃው ዩራኒየም በትንሹ ከበለፀገ ለቤት ውስጥ መብራትና ለፋብሪካዎች ኃይል ይሰጣል። ከፍተኛ ደረጃው ዩራኒየም በጣም ከበለፀገ ግን ወደ “ኑክሌር ቦምብ” ይቀየራል።
ኢራን ከፍተኛ መጠን ያለው ዩራኒየም አከማችታለች። አሜሪካ ደግሞ “ይህ ክምችት ወደ ቦምብ ሊቀየር ይችላል” የሚል ስጋት አላት ለዚህም ነው ትራምፕ “ኢራን ክምችቱን አሳልፋ ትስጥ” የሚል ግፊት የሚያደርጉት። ኢራን ግን “ለሃይል ማመንጫ ስለምፈልገው ክምችቱን አሳልፌ አልሰጥም” እያለች ነው።
ሁለቱ ሀገራት ለሰላም ድርድር እየተዘጋጁ ቢሆንም ይህ የዩራኒየም ክምችት ጉዳይ ግን ድርድሩን ከባድ ሊያደርገው እንደሚችል ተገምቷል። ኢራን “አልሰጥም” ማለቷ በአሜሪካ በኩል ተጨማሪ ማዕቀቦች ሊመጡ እንደሚችሉ ፍንጭ እየሰጠ ነው።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: