የዓለም ነዳጅ ዋጋ ናረ

- Advertisement -
Sidebar AD

* የጦርነት ደመና በመካከለኛው ምስራቅ እያንዣበበ ነው!

#Ethiopia | ​ዓለም አቀፉ የፖለቲካ ውጥረት የኢኮኖሚ ቀውስ እየወለደ ነው! በመካከለኛው ምስራቅ የተቀሰቀሰው ወታደራዊ ፍጥጫ ዛሬ አርብ የነዳጅ ዋጋን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር አድርጎታል።

​ብሬንት ነዳጅ (Brent Crude)፦
በ1.17% በመጨመር አንድ በርሜል $106.3 ደርሷል።

​WTI ነዳጅ፦
በ1.12% አድጎ $96.92 ሆኗል።

​ የኢራን ኮማንዶዎች በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የንግድ መርከብ መቆጣጠራቸውና በቴህራን ሰማይ ላይ የአየር መከላከያ ሚሳይሎች ተኩስ መጀመሩ ስጋቱን ከፍ አድርጎታል።

በአሜሪካና በኢራን መካከል ያለው ድርድር መቋረጡን ተከትሎ፣ ተንታኞች አሁን ያለው ሁኔታ “ወደ ጦርነት ለመግባት የሚደረግ የዝግጅት ምዕራፍ” እንደሆነ እያስጠነቀቁ ነው። ግጭቱ በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ የነዳጅ ዋጋ የዓመቱን ከፍተኛ ጣራ (Record) ሊሰብር እንደሚችል ተገምቷል።

ይህ የነዳጅ ዋጋ ንረት በቀጥታ ወደ ኪሳችን ነው የሚመጣው። የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት ማለት የዓለም ኢኮኖሚ መታፈን ማለት ነው። ትራምፕና የኢራን መሪዎች ለዚህ ፍጥጫ ምን ዓይነት መፍትሄ ይሰጡ ይሆን? ወይስ ዓለም ሌላ ጦርነት ልታስተናግድ ነው?

​የነዳጅ ዋጋው ከጦርነቱ ድምጽ በላይ እየጮኸ ነው!

​#getu #OilPriceSpike #MiddleEastConflict #IranVsUSA #HormuzStrait #GlobalEconomy #BreakingNews #EnergyCrisis #ነዳጅ #የነዳጅዋጋ #ኢራን #ጦርነት #ኢኮኖሚ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1