ናይጄሪያዉያን የሚናገሩት እንግሊዘኛ ቋንቋ ለመረዳት የማይቻል እና ተርጓሚ ያስፈልገዋል ሲሉ የኬንያ ፕሬዝዳንት መናገራቸዉን ተከትሎ ተቃዉሞ ገጠማቸዉ
የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የናይጄሪያ ዜጎች የሚናገሩት እንግሊዝኛ ቋንቋ ለመረዳት የማይቻል እና ተርጓሚ ያስፈልገዋል ብለው በይፋ ከገለጹ በኋላ በማህበራዊ ሚዲያ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።ሰኞ እለት በጣሊያን ለሚኖሩ ኬንያውያን ንግግር ያደረጉት ሩቶ ናይጄሪያዊ ሲናገሩ የምትሰሙ ከሆነ የሚናገሩትን አታውቁም ፤ተርጓሚ ያስፈልጋችኃል በማለት ኬንያውያን “በአለም ላይ ካሉ ምርጥ እንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው” ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ይህ ንግግራቸዉ ግን የአፍሪካን ሀገር አዋርደዋክ ሲሉ የተቹት ናይጄሪያውያን እና ሌሎች አፍሪካውያን በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከፍተኛ ውግዘት አስከትሏል።የዚምባብዌ ጋዜጠኛ ሆፕዌል ቺኖኖ “እንግሊዘኛ የቅኝ ግዛት ቋንቋ እንጂ የእውቀት፣ የችሎታ ወይም የሀገር እድገት መለኪያ አይደለም” ሲል ጽፏል።
የቀድሞ የብሪታንያ ቅኝ ግዛቶች የሆኑት ሁለቱም ኬንያ እና ናይጄሪያ እንግሊዘኛን እንደ ይፋዊ ቋንቋ ይጠቀማሉ፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ሀገር የተለያየ የፎነቲክ አወቃቀሮች ያሏቸው የተለያዩ የንግግር ዘዬን አዘጋጅተዋል።እነዚህ ልዩነቶች የአገሬው ተወላጆችን ተፅእኖ የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ ናይጄሪያ ከ 500 በላይ ቋንቋዎች ያሏት ሲሆን ኬንያ ደግሞ ባንቱ ፣ ኒሎቲክ እና ኩሺቲክ ድብልቅ የራሷን የእንግሊዘኛ ንግግሮች ያስገኛሉ።
ነገር ግን ሩቶ ለዲያስፖራዎች ስብስብ ባደረጉት ንግግር የኬንያ የትምህርት ስርዓት ጠንካራ የእንግሊዘኛ ቋንቋን ያዳብራል በማለት ናይጄሪያውያን እንግሊዝኛ ሲናገሩ ለመረዳት አዳጋች ነው ብለዋል።
@seledadotio

No comments yet.