እስራኤል እና ሊባኖስ የተኩስ አቁም ስምምነቱን በሦስት ሳምንታት ለማራዘም ተስማምተዋል ሲሉ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሳውቀዋል።ስምምነቱ የመጣው የእስራኤል እና የሊባኖስ ባለሥልጣናት ዋይት ሀውስ ውስጥ ያልተለመደ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ ነው።
በጎርጎሪዮሱ የካቲት 28 ቀን፣ እስራኤል በኢራን ላይ የጋራ ጥቃት ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ፣ በተለይም በደቡብ እና በዋና ከተማዋ ቤሩት ላይ የአየር ድብደባ ስትፈጽም ቆይታለች።እስራኤል ጥቃቱ በሊባኖስ ውስጥ የሒዝቦላህ መቀመጫ ቦታዎችን እና ምሽጎችን ዒላማ ያደረገ መሆኑን ገልፃለች።
ሒዝቦላህ በዩናይትድ ስቴትስ፤ ጀርመን እና በርካታ የሱኒ ዐረብ ሃገራት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ፤ በኢራን የሚደገፍ የሊባኖስ የሺዓ ፖለቲካ ፓርቲ እና ወታደራዊ ክንፍ ነው ። በጎርጎሪዮሱ 1982 በሊባኖስ የእርስ በርስ ጦርነት (1975-1990) እና በእስራኤል የደቡብ ሊባኖስ ወረራ ወቅት ብቅ ያለ ቡድን ነው። ሒዝቦላህ የፖለቲካ እና የትጥቅ ቡድን ሲሆን፤በ1979 በኢራን የእስልምና አብዮት መሰረት በነበረው የሺዓ እስላማዊ ርዕዮተ ዓለም ደጋፊ ነው። ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮም በኢራን የእስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ድጋፍ፣ ስልጠና እና መሣሪያ ያገኛል።
ቡድኑም ለትልቋ ለጋሽ ሀገር ለኢራን ወኪል ሆና ይሰራል። የአሜሪካ መንግስት በጎርጎሪያኑ 2023 መጨረሻ ባወጣው መረጃ ኢራን ለሒዝቦላህ በየዓመቱ ወደ 700 ሚሊዮን
ዶላር (661 ሚሊዮን ዩሮ) ትሰጣለች ተብሎ ይገመታል።
DW Amharic
Source: Yeneta Tube









No comments yet.