ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የዳሰሳ ጥናት የሚያከናውኑ ባለሙያዎች እንደሚሰማሩ ተገለጸግንቦት 2…

- Advertisement -
Sidebar AD
ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ የፀጥታ ችግር ባለባቸው አካባቢዎች የዳሰሳ ጥናት የሚያከናውኑ ባለሙያዎች እንደሚሰማሩ ተገለጸ
ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም በሚከናወነው ምርጫ ላይ የፀጥታ ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች ለመለየት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚሰሩ ያስታወቀው የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ነው።
የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ ሜላትወርቅ ኃይሉ እንደገለጹት፤ በጸጥታ ስጋት ቀጠናዎች ያሉ አስቻይ ሁኔታዎችን መለየት እንዲቻል ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሲቪል ማኅበራት የተውጣጡ አካላትን ማዘጋጀት ተችሏል። ይህ ዓይነቱ አሰራር በተለይ ስጋት ያለባቸውን ቦታዎች ለመለየትና የፖለቲካ ምህዳሩን ለመመልከት እንደሚያመች በመጠቆም፣ በቀጣይ ሳምንት እንቅስቃሴዎች እንደሚጀመሩ አስታውቀዋል።
በሌላ በኩል በትግራይ ክልል ምርጫን ለማካሄድ አሁንም ጥረቶች እየተደረጉ መሆኑን የጠቀሱት ሰብሳቢዋ፣ የአስቻይ ሁኔታዎች መፈጠር ለምርጫውም ሆነ ለሕዝቡ አስፈላጊ በመሆኑ በትኩረት ይሰራበታል ብለዋል። በተጨማሪም ለምርጫው አጋዥ የሆኑ ቁሳቁሶችን የማጓጓዝ እና ግብዓቶችን የማሟላት ስራ መከናወኑን አስረድተዋል።
ሰባተኛው አገራዊ ምርጫ ለመካሄድ ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርተውታል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: