የታሸገ ውሃ የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ ቀውስ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ
በቅርቡ በታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ በዓለም አቀፍ አለመረጋጋት የተፈጠረ እንጂ በሀገር ውስጥ ካለው የምርት አቅርቦት ጋር የተያያዘ አለመሆኑን በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪ ምርምርና ልማት ማዕከል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደበበ ወርቁ ለመናኸሪያ ሬዲዮ ተናግረዋል።
የታሸገ ውሃ አምራቾች የጥሬ ዕቃ ግብዓቶችን ከውጭ ሀገራት የሚያስገቡ በመሆኑ፣ አሁን ላይ ግብዓቶቹን በሚፈለገው መጠን ማስገባት አለመቻሉን ሥራ አስኪያጁ ገልጸው፤ በዚህም ምክንያት በምርቶች ላይ የዋጋ ጭማሪ መታየቱን አስረድተዋል።
ቀደም ሲል በታሸገ ውሃ አምራቾች በኩል የሚነሱ የውጭ ምንዛሬ እና የግብዓት አቅርቦት ጥያቄዎች ምላሽ አግኝተው፣ በአሁኑ ወቅት ከአንድ መቶ በላይ አምራቾች ወደ ዘርፉ መቀላቀላቸውን ሥራ አስኪያጁ አስታውሰዋል። ያሉት አምራቾችም በሙሉ አቅማቸው እየሰሩ በመሆኑ ከአቅርቦት ጋር የተያያዘው ችግር መፈታቱን አብራርተዋል።
በቅርቡ በሁሉም የታሸጉ የውሃ ምርቶች ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ ወቅታዊ መሆኑን የገለጹት አቶ ደበበ፣ የዓለም አቀፍ ገበያው ሲረጋጋ ችግሩ እንደሚቀረፍ አመልክተዋል።
በመጨረሻም በ”ኢትዮጵያ ታምርት” ንቅናቄ ወደ ዘርፉ የሚገቡ አምራቾች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ጠቅሰው፤ በምርት ሂደት ላይ የሚታዩ የዋጋ፣ የጥራት እና መሰል ችግሮች እንዲፈቱ ተቋሙ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
@seledadotio

No comments yet.