የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በባይራ አክሲዮን ማኅበር ላይ የማስጠንቀቂያ ውሳኔ አስተላለፈ

- Advertisement -
Sidebar AD

የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን ባይራ አክሲዮን ማኅበር እያከናወነ ያለው የአክሲዮን ሽያጭ ሕገ-ወጥ መሆኑን በመግለጽ፣ ሕብረተሰቡ ከግዢ እንዲቆጠብ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ ሰጠ።

ባለሥልጣኑ ባደረገው ክትትል ድርጅቱ ‘አርባ ምንጭ ውሃ’ በሚል ስያሜ የውሃ ፋብሪካ ለማቋቋም ሳይመዘገብ አክሲዮኖችን በማኅበራዊ ሚዲያና በተለያዩ አማራጮች ለሽያጭ ሲያቀርብ መቆየቱ ተደርሶበታል።

ይህ ድርጊት የካፒታል ገበያ አዋጅ ቁጥር 1248/2013 እና የሰነደ መዋለ ንዋዮችን መመሪያ በግልጽ የጣሰ መሆኑን ባለሥልጣኑ አስታውቋል።

ማንኛውም ድርጅት አክሲዮን ለሕዝብ ይፋ ከማድረጉ በፊት በባለሥልጣኑ መመዝገብና የቅድመ-ማስታወቂያ ፈቃድ ማግኘት የሚጠበቅበት ቢሆንም፣ ባይራ አክሲዮን ማኅበር ግን ይህንን ሕጋዊ ሂደት ሳይከተል ወደ ሽያጭ መግባቱ ተገልጿል።

ድርጊቱ በሕግ ፊት በወንጀል የሚያስጠይቅ በመሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በድርጅቱ ላይ ጥልቅ አስተዳደራዊ ምርመራ እየተከናወነ ይገኛል።

የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች (ኢንቨስተሮች) መብት ለማስጠበቅ አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ የጠቆመው ባለሥልጣኑ፣ ሕብረተሰቡ ለማንኛውም የሽያጭ ወኪልም ሆነ በቀጥታ ለድርጅቱ ምንም ዓይነት ክፍያ እንዳይፈጽም አሳስቧል።

መሰል ተግባራት ሲያጋጥሙ ማኅበረሸቡ ጥቆማ እንዲሰጥ የጠየቀው ባለሥልጣኑ፣ ማንኛውም አካል ገንዘብ ከመክፈሉ በፊት ተቋማቱ በሕግ የተመዘገቡ መሆናቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አሳስቧል።

#አሐዱ


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: