ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ጋር ተወያዩ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር ማያርዲትን ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብሔራዊ ቤተመንግሥት ተቀብለው አነጋግረዋል።

ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኬር በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት የሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን፣ በቆይታቸውም ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

እንደ መርሃ ግብሩ መግለጫ፣ የመሪዎቹ ምክክር ትኩረት የሚያደርገው በሁለቱ ጎረቤት አገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣ በጸጥታ፣ በንግድ እና በጋራ የልማት መስኮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ነው።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1