የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በ9 ወር 10 ቢሊዮን ብር ገቢ ሰበሰበ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈፃፀሙን በገመገመበት ወቅት፣ ተቋማዊ ሪፎርሙን ተከትሎ እጅግ አስደናቂ ውጤቶችን ማስመዝገቡን አስታውቋል። ኮርፖሬሽኑ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ56 በመቶ የገቢ ዕድገት አሳይቷል።

​በ9 ወራት ውስጥ ከ10 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል። ይህም ካለፈው ዓመት የ3.4 ቢሊዮን ብር ብልጫ አለው።

​በርዝመቱ ትልቁ የሆነው ባለ 27 ወለል የሱማሌ ተራ ሕንፃ እና በፒያሳ ለወርቅ ቤቶች ተብሎ የታሰበው ዘመናዊ ሞል ግንባታ ተጠናቅቀው ተመርቀዋል።

​ ለመጀመሪያ ጊዜ የ3ዲ (3D) ኮንክሪት ግንባታ ቴክኖሎጂ ወደ ሀገር ውስጥ ገብቶ በሙከራ ላይ ይገኛል።

​ በልማት ምክንያት የፈረሱ 731 ሱቆች በ”ዜሮ ኢንቨስትመንት” ተገንብተው ለደንበኞች ተላልፈዋል።

የኮንክሪት ውጤቶች (ብሎኬትና ታይልስ) ለገበያ በስፋት እየቀረቡ ሲሆን፣ በሪል ስቴት ዘርፉም ቤቶችን በአጭር ጊዜ ገንብቶ በማስረከብ ታማኝነቱን አረጋግጧል።

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የ50 ዓመት ጉዞውን በወርቅ ኢዮቤልዩ እያከበረ፣ እንዲህ ያለ የገቢና የቴክኖሎጂ ስኬት ማስመዝገቡ ለሀገራችን የግንባታ ዘርፍ ትልቅ ተስፋ ነው።

በተለይ የ3D ግንባታ ቴክኖሎጂ የቤቶችን ችግር በአጭር ጊዜ ለመፍታት ወሳኝ ሚና ይኖረዋል።

​ከአሮጌው አሰራር ወደ ዘመናዊው የግንባታ ምዕራፍ!

​#getu #FederalHousingCorporation #EthiopianConstruction #HousingDevelopement #3DConstruction #UrbanRenewal #AddisAbabaCorridor #BreakingNews #FHC #ኢትዮጵያ #ቤቶችኮርፖሬሽን #ግንባታ #ሪፖርት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: