ጠ/ሚ ኔታንያሁ የካንሰር ህክምና ሲያደርጉ መቆየታቸውን በይፋ አመኑ

- Advertisement -
Sidebar AD

* ኦፕሬሽኑና ሚስጥሩ

#Ethiopia | ​የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ ላለፉት ጥቂት ወራት በካንሰር ህመም ሲሰቃዩና ህክምና ሲያደርጉ እንደነበር ዛሬ አርብ በይፋ አስታወቁ። የ76 ዓመቱ መሪ ይህንን ሚስጥር ለምን ደበቁ? አሁንስ የጤና ሁኔታቸው በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

በመጀመሪያ ደረጃ ላይ የሚገኝ የፕሮስቴት ካንሰር (Prostate Cancer) ተገኝቶባቸው እንደነበር ገልጸዋል።

እ.ኤ.አ በ2024 ማጠናቀቂያ ላይ ቀዶ ጥገና ካደረጉ በኋላ፣ በኢየሩሳሌም በሚገኘው ሀዳሳህ የህክምና ማዕከል የተሳካ ህክምና ተደርጎላቸዋል።

ከኢራን ጋር በነበረው ከፍተኛ የጦርነት ወቅት በሀገሪቱ ላይ ስጋት እንዳይፈጠርና ትኩረት እንዳይከፋፈል በማሰብ መረጃው ሚስጥር ሆኖ እንዲቆይ መደረጉን ጠቁመዋል።

ኔታንያሁ አሁን ካንሰሩ ሙሉ በሙሉ እንደጠፋና “በጣም በጥሩ የጤና ሁኔታ ላይ እገኛለሁ” ሲሉ ለህዝባቸው አረጋግጠዋል።

ይህ መግለጫ የወጣው፣ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የታገዙና “ኔታንያሁ ሞተዋል” የሚሉ የሀሰት ቪዲዮዎችና ወሬዎች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተሰራጭተው በነበረበት ወቅት መሆኑ ጉዳዩን ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጎታል።

ኔታንያሁ በጦርነትና በህመም መካከል ሆነው እስራኤልን መምራታቸው ለብዙዎች አስገራሚ ሆኗል። ህመማቸውን ደብቀው ጦርነቱን መምራታቸው “የመሪነት ብቃት ወይስ ህዝብን መደበቅ?” በሚል ለክርክር በር ከፋች ነው። የእርሳቸው ማገገም በመካከለኛው ምስራቅ ሰላም ላይ ምን ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን?

​ህመማቸውን በጦርነት የሸፈኑት መሪ—ኔታንያሁ በካንሰር ላይ ድል ተቀዳጁ!

​#getu #Netanyahu #IsraelNews #CancerSurvivor #BreakingNews #MiddleEastPolitics #Healthcare #NetanyahuHealth #እስራኤል #ኔታንያሁ #ካንሰር #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: