ቀዳሜ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስ ከታላቁ የአይሁድ መምህር ገማልያል ከተማሩና ሰፊ እውቀት ካላቸው አርድዕት አንዱ ነው፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

በመጀመሪያ የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ሲሆን ጌታችን ሲመጣ እርሱን ተከትሏል፡፡ ከጌታ ዕርገት በኋላ ቅዱሳን ሐዋርያት መንፈስ ቅዱስን ሲቀበሉም ጸጋው በዝቶ ከታደሉት አንዱ ነበር፡፡ 8 ሺውን የክርስቲያን ማኅበር እንዲመሩ ሰባት ዲያቆናት ሲሾሙም ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት ሆኗል፡፡ ወንጌልን እየሰበከ ሲጋደል አይሁድ ትምህርቱን ቢሳናቸው ክርስትናን ለማጥፋት እርሱን መግደል እንዳለባቸው ስላመኑ በድንጋይ ወግረው ሲገድሉት ፊቱ እንደ እግዚአብሔር መልአክ እያበራ ወልድን በአብ ቀኝ ይመለከተው ነበር። ስለ ወጋሪዎቹ ምሕረትን ሲለምን ሰማያዊ የሰማዕትነት አክሊል ተቀዳጀ።

ቅዱስ እስጢፋኖስ ከአረፈ ከ300 ዓመት በኋላ በኢየሩሳሌም የሚኖር ሉኪያኖስ የተባለ ደግ ሰው በተደጋጋሚ በራዕዪ እየተገለጸለት “ሥጋዬን አውጣ” ሲለው ለጳጳሱ ነገራቸው። ጳጳሱም ካህናትና ምዕመናንን ሰብስበው ወደ አፀደ ገማልያል ማለት ወደ መምህሩ ሄደ። ቦታውንም በቆፈሩ ጊዜ ታላቅ መነዋወጥ ሆነ። መላዕክት ሲያጥኑም በጎ መዓዛ ሸተተ። ዝማሬ መላዕክትም ተሰማ። ሕዝቡና ጳጳሱም በቅዱስ እስጢፋኖስ ፊት ሰግደው በታላቅ ዝማሬና በሐሴት ዐፅሙን ከዚያ አውጥተው በጽርሐ ጽዮን በተቀደሰችው ቤት አኖሩት። እለ እስክንድሮስ የተባለ ደግ ሰውም ቤተክርስቲያን አነጸለት ወደዚያ አገቡት።

ከአምስት ዓመታት በኋላም እስክንድሮስ ሲያርፍ በሳጥን አድርገው በቅዱሱ ጎን አኖሩት። የእለ እስክንድሮስ ባለቤት ግን ወደ ሀገሩዋ ቁስጥንጥኒያ ስትመለስ የባሏ ሥጋ መስሉዋት የቅዱስ እስጢፋኖስን ቅዱስ ሥጋ በመርከብ ጭና ወሰደችው። መንገድ ላይም ከሳጥኑ ውስጥ ዝማሬ ሰምታ ብታየው ያመጣችው የቅዱሱን ሥጋ ነው። እጅግም ደስ አላት አምላክ ለዚህ አድሉዋታልና። እርሷም ወስዳ ለታላቁ ንጉሥ ቅዱስ ቆስጥንጢኖስ አስረከበችው። በከተማው ታላቅ ሐሴት ተደረገ። ሥጋውን ሊያኖሩት በበቅሎ ጭነው ሲወስዱትም በቅሎዋ በሰው ልሳን ተናግራ ማረፊያውን አሳወቀች። በዚያም ላይ ትልቅ ቤተክርስቲያን ታንጾለታል። ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አሳልፈው የሰጡ ቅዱሳንና ሰማዕታትን የሚዘክሩ በአማላጅነታቸው የሚማጸኑ ገዳማውያን በረከታቸው የበዛ ነው፡፡ ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፣ ከበረከታቸው እንካፈል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1