በዘንድሮው ዓመት የሺህ ጋብቻ መርሃ ግብር እንደማይካሄድ ተገለጸ
የሺህ ጋብቻ በያሜንት ኃ.የተ.የግ.ማ. የሚዘጋጅና በሺዎች የሚቆጠሩ ጥንዶች በአንድነት የሚዳሩበት የጋራ የሰርግ ክብረ በዓል መሆኑ ይታወቃል። ከኢትዮጵያም አልፎ አፍሪካውያን ይሳተፉበታል ተብሎ በሚጠበቀው የዘንድሮው የ2018 ዓ.ም የሺህ ጋብቻ ክብረ በዓል እንደማይካሄድ ተገልጿል።
መርሃ ግብሩ የማይካሄድበትን ምክንያት በተመለከተ መናኸሪያ ሬዲዮ ባደረገው የማጣራት ሂደት ሁለት ዓይነት ምላሾችን አግኝቷል።
የሺህ ጋብቻ መርሃ ግብርን ለማዘጋጀት ይደረግ የነበረው እንቅስቃሴ ከ4 ወራት በፊት መቆሙን የገለጹት፣ ቀደም ሲል በማህበሩ የኮንቴንት ፕሮዳክሽን ዳይሬክተር የነበሩት አቶ ሰለሞን አበራ፤ የመርሃ ግብሩ ባለቤቶች ለጊዜው ሥራውን መቀጠል እንደማይችሉና ሠራተኞችም በሥራ ገበታቸው ላይ እንዳልሆኑ ለመናኸሪያ ሬዲዮ አስታውቀዋል።
አቶ ሰለሞን ባላቸው መረጃ መሠረት፥ በማህበሩ የሚሰሩ ባለሙያዎች “ስንፈልጋችሁ እንጠራችኋለን” ተብለው እንዲበተኑ የተደረገው በበጀት እጥረትና በመሰል ችግሮች ምክንያት ነው።
በዚሁ ጉዳይ ላይ ጣቢያው ያነጋገራቸው የያሜንት ኃ.የተ.የግ.ማ. ጸሐፊ ሂሩት አበበ በበኩላቸው፤ የማህበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚና የሺህ ጋብቻ ፕሮግራም አስተባባሪ አቶ አስናቀ አማኑኤል ባጋጠማቸው ድንገተኛ የጤና እክል ምክንያት የዘንድሮው መርሃ ግብር እንደማይካሄድ ለመናኸሪያ ሬዲዮ 99.1 ገልጸዋል።
ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ የተካሄደው ይህ መርሃ ግብር፣ በቀጣይ ዓመት ከመስከረም ጀምሮ ዝግጅቱን እንደሚጀምር ይጠበቃል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.