ቴዲ አፍሮ የኢትዮጵያን የሙዚቃ ሰንጠረዥ ለ2ኛ ሳምንት ተቆጣጠረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja | በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲሱን አልበሙን ተከትሎ የሳምንቱን የሙዚቃ ሰንጠረዥ በበላይነት መርቷል። ከሚያዝያ 9 እስከ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በ”የኔ ቫይብ” ይፋዊ የሙዚቃ ደረጃ መሠረት፣ በሳምንቱ ከፍተኛ እይታ ካገኙ 10 ሙዚቃዎች ውስጥ ዘጠኙን የቴዲ አፍሮ የ”ኢትዮሪካ” አልበም ስራዎች ይዘውታል።

በተለይም “ዳስ ጣል (አንሳው)” የተሰኘው ስራው በአንድ ሳምንት ውስጥ ብቻ ከ11 ሚሊዮን በላይ አዳዲስ ተመልካቾችን በማግኘት ቀዳሚነቱን የያዘ ሲሆን፣ አጠቃላይ የእይታ መጠኑንም ወደ 16.6 ሚሊዮን አሳድጓል። ይህ አሃዝ በሀገሪቱ የዲጂታል የሙዚቃ ስርጭት ታሪክ ውስጥ አዲስ ክብረ ወሰን መሆኑ ተመልክቷል።

በቴዲ አፍሮ ስራዎች በተጥለቀለቀው በዚህ ሰንጠረዥ ውስጥ ብቸኛው ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት ገላና ጋሮምሳ እና ዮሳን ጌታሁን በጋራ የተጫወቱት “ጋልሜ ሴና” የተሰኘው አዲስ የኦሮምኛ ሙዚቃ ሲሆን፣ በሳምንቱ 2.4 ሚሊዮን እይታዎችን በማግኘት 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሙዚቃ ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ የቴዲ አፍሮ ስራዎች እንዲህ ባለው ፍጥነት በሚሊዮኖች መታየታቸው የአርቲስቱን የቆየ ተወዳጅነት ከማሳየቱም በላይ፣ የኢትዮጵያ የዩቲዩብ ተጠቃሚዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን ማሳያ ነው። ደረጃው የተሰላው ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ አውቶማቲክ ሲስተም መሆኑ ተዓማኒነቱን ከፍ አድርጎታል።

የሳምንቱ ምርጥ 10 የሙዚቃ ደረጃዎች ዝርዝር፦
1. ዳስ ጣል (አንሳው) – ቴዲ አፍሮ (+11.3 ሚሊዮን እይታ)
2. ስምምነን (ጉሬጌ) – ቴዲ አፍሮ (+5.2 ሚሊዮን እይታ)
3. ሺ ቢባል (ወደ 90ዎቹ) – ቴዲ አፍሮ (+4.5 ሚሊዮን እይታ)
4. ጀምበር – ቴዲ አፍሮ (+3.9 ሚሊዮን እይታ)
5. ዝ ፀዳል – ቴዲ አፍሮ (+3.7 ሚሊዮን እይታ)
6. መሬማ – ቴዲ አፍሮ (+3.5 ሚሊዮን እይታ)
7. መርከብ – ቴዲ አፍሮ (+3.2 ሚሊዮን እይታ)
8. ጽዮን ሙሽራዬ – ቴዲ አፍሮ (+3.0 ሚሊዮን እይታ)
9. ብልጭታ – ቴዲ አፍሮ (+2.8 ሚሊዮን እይታ)
10. ጋልሜ ሴና – ገላና ጋሮምሳ እና ዮሳን ጌታሁን (+2.4 ሚሊዮን እይታ)


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2