ቻይና ድሮኖችን በቅጽበት የሚያመከን አዲስ የሌዘር መሣሪያ ለገበያ አቀረበችዘመናዊው ዓለም እየተከተለ ያለውን የድሮን ውጊያ ስል…

- Advertisement -
Sidebar AD
ቻይና ድሮኖችን በቅጽበት የሚያመከን አዲስ የሌዘር መሣሪያ ለገበያ አቀረበች
ዘመናዊው ዓለም እየተከተለ ያለውን የድሮን ውጊያ ስልት ለመቀየር ቻይና በዋጋው ተመጣጣኝና በፈጣንነቱ ተወዳዳሪ የሆነ አዲስ የሌዘር መሣሪያ ይፋ አደረገች። NI-L3K የተሰኘው ይህ የላዘር መሣሪያ በተለይም አነስተኛና ፈጣን ድሮኖችን በመምታት ረገድ ከፍተኛ ብቃት እንዳለው ተነግሮለታል። በራዳር እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎች ላይ በሚሠራው ኖቫስኪ ቴክኖሎጂ ኩባንያ የተመረተው ይህ መሣሪያ እስከ 4,500 ጫማ ርቀት ላይ የሚገኙ ድሮኖችን በሌዘር ጨረር የመምታት አቅም አለው።
ይህ ሲስተም ባለ 3 ኪሎ ዋት የላዘር ኃይል እና እስከ አንድ ማይል ርቀት ድረስ ድሮኖችን በራሱ መለየትና መከታተል የሚችል ዘመናዊ ካሜራ ተገጥሞለታል።
መሣሪያው በቀላሉ በትንንሽ ፒካፕ ተሽከርካሪዎች ላይ ተጭኖ የሚንቀሳቀስ በመሆኑ በጦር ግንባር፣ በወታደራዊ ካምፖች እና በቁልፍ ሕንፃዎች አካባቢ በፍጥነት አሰማርቶ ለመጠቀም እጅግ ምቹ ነው።
የNI-L3K የሌዘር ሲስተም እ.ኤ.አ. በ2025 በፓሪስ እንዲሁም በ2026 በማሌዢያ በተካሄዱ ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ዓውደ ርዕዮች ላይ ለዕይታ ቀርቧል። አምራች ኩባንያው መሣሪያውን ለተለያዩ የዓለም ሀገራት ለመሸጥ ማቀዱን ያስታወቀ ሲሆን ይህ ግኝት ሀገራት ውድ የሆኑ ሚሳይሎችን ከመጠቀም ይልቅ ድሮኖችን በአነስተኛ ወጪ ለማክሸፍ የሚያደርጉትን ጥረት የሚያግዝ ነው ተብሏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: