“ወደ 1ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ክፍያ ፈፅመናል”- ምርጫ ቦርድ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ለፖለቲካ ፓርቲዎች በሚደረገው የገንዘብ ድጋፍ መሰረት እስካሁን 81 ሚሊዮን ብር ክፍያ መፈጸሙም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ሀይሉ የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቅን አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ላይ ጠቅሰዋል።

ሰብሳቢዋ እንደገለፁት “የመጀመሪያውን 30 በመቶ የፓርቲ የምርጫ ጊዜ ድጋፍ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ከ 1 ወር በፊት አከፋፍለናል፤ዛሬ ደግሞ የሚቀጥለውን ክፍያ 32 ለሚሆኑ የንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር ላላቸው ፓርቲዎች ቦርዱ በድምሩ 81 ሚሊየን ብር አሰራጭቷል” ብለዋል ።

ሰብሳቢዋ አያይዘውም፤ ከንግድ ባንክ ውጭ ላሉት ፓርቲዎች የሚደረገው የገንዘብ ዝውውር የራሱ ሂደት ስላለው እያከታተልን እናስገባለን በማለት አክለዋል።

የፓርቲዎች ክፍያ የሚያተኩረው ባቀረቧቸው እጩዎች፣ሴት እጩዎች፣አካል ጉዳተኛ እጩዎች እና ሴት አካል ጉዳተኛ አጩዎች ልክ መሆኑን ነው ያነሱት።

የምርጫ በጀትን በተመለከተ መንግስት 10ቢሊየን ብር የመደበ ቢሆንም፤ አሁን ካለው አካሄድ አኳያ ቦርዱ ከተበጀተው በጀት በላይ ያሰፈልጋል ብሎ በማመኑ የተጨማሪ በጀት ጥያቄ ማቅረብን ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ገልፀዋል።

ሰብሳቢዋ ወደ 195 ሺ 316 ከሚሆኑ ምርጫ አስፈፃሚዎች 70 ሺ በላይ ለሚሆኑ ምርጫ አስፈፃሚዎች ወደ 1ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ክፍያ ፈፅመናል ብለዋል።

ምንም እንኳ በምርጫ ቦርዱ እና ምርጫ አስፈፃሚዎች መካከል ባለው ውል መሰረት የመጀመሪያው 40 በመቶ ክፍያ የሚፈፀመው የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ ከ 15 ቀናት በኋላ ቢሆንም፤ ቦርዱ ያለውን ሁኔታ በመመልከት ቀደም ብሎ ክፍያ መፈፀሙን አስታውቀዋል።

ለቀሪ ምርጫ አስፈፃሚዎች የዳታ ማጣራት ተደርጎ በትክክለኛው አካውንታቸው ላይ ክፍያ እንደሚፈፀም አክለዋል።

በምርጫ ምዝገባ ሂደት ውስጥ አብዛኞቹ ምርጫ አስፈፃሚዎች ስራቸውን በአግባብ ማከናወናቸውን ጠቁመዋል።

የምዝገባ ሂደቱን ባስተጓጎሉ ምርጫ አስፈፃሚዎች ላይ ተገቢው እርምጃ መወሰዱንም የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሜላተወርቅ ኃይሉ ገልፀዋል ሲል ቲክቫህ ዘግቧል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1