”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” ጅማ ከተማ ደረሰ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እና የቱሪዝም ሚኒስቴር ጥምረት የሆነው ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህቦች በስፖርት ለማስተዋወቅ አልሞ ስድስት ከተሞችን የሚያዳርስ የሩጫ እና የጉብኝት መርሃ-ግብር እያከናወነ ይገኛል።

​የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ስራ አስኪያጅ ሃና ገብረሥላሴ እንደገለጹት፤ የ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ” ዋና ትኩረት ኢትዮጵያ በስፖርት ያላትን ዝና በመጠቀም የቱሪዝም ገጽታዋን ለዓለም ማስተዋወቅ ነው።

ባለፈው ጊዜ ደብረ ብርሃን እና ሀዋሳ በደማቅ ሁኔታ የተከናወነው ”ልወቅሽ ኢትዮጽያ” የሩጫ መርሃ ግብር ”ታላቁ ሩጫ በጅማ” ተብሎ በጅማ ከተማ ነገ ይከናወናል።

​ውድድሩ በየወሩ የሚከናወን ሲሆን፣ ከየካቲት እስከ ሐምሌ ለስድስት ወራት የሚቆይ ነው። የከተሞቹ ምርጫ ኢትዮጵያን በሁሉም አቅጣጫዎች ከማወቅና ከተሞቹ ካላቸው ልዩ ስፖርታዊ እና ተፈጥሯዊ እሴት አንጻር የተደረገ ነው።

ለአብነት ​በቆጂ የአትሌቶች መገኛ በመሆኗ፤​አርባ ምንጭ የተፈጥሮ ጥበቃን ለማስተዋወቅ፤ ​ጅማ የቡና መገኛ መሆኗን እና ተፈጥሮዋን ለማሳየት ተመርጠዋል።

በነገው ዕለት ​በጅማ ከተማ በሚካሄደው የ5 ኪሎ ሜትር የህጻናት እንዲሁም የ 15 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ከ4,000 በላይ ተሳታፊዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከ600 በላይ ታዳጊዎችም በተለያዩ የእድሜ እርከኖች ይሳተፋሉ። በተጨማሪም ከአዲስ አበባ እና አካባቢዋ የመጡ 120 የሚሆኑ ሯጮች ውድድሩ ላይ ለመካፈል ጅማ ደርሰዋል ተብሏል።

​ከሩጫው ባሻገር፣ ተሳታፊዎች በሆራይዘን ፕላንቴሽን ጉብኝት በማድረግ ስለ ቡና አመራረት “ከእርሻ እስከ ሲኒ” ያለውን ሂደት እንዲገነዘቡ ተደርጓል። ይህም ስፖርቱን ከቤተሰባዊ መዝናኛ እና ከሃይኪንግ ጋር በማቀናጀት ለተሳታፊዎች የተለየ ተሞክሮ የፈጠረ ነበር።

​መርሃ-ግብሩ በደብረ ብርሃን እና ሐዋሳ የተሳካ ቆይታ አድርጓል ፤ በነገው ዕለትም ጅማ ተረኛ ስትሆን በቀጣይ ወራት ወደ በቆጂ እና አርባ ምንጭ በማምራት ማጠቃለያውን በታሪካዊቷ ሐረር ከተማ ላይ እንደሚያደርግ ታውቋል።

ለ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያናኮሙዩኒኬሽንስ

ያፌት ገ/ህይወት
ከጅማ ዞን ፤ ጅማ ከተማ





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: