( ከደንቢ ዶሎ እስከ ~ ሚዛን – ተፈሪ )

- Advertisement -
Sidebar AD

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ~ ነጋሶ ጊዳዳ ( ዶ.ር )

ምዕራፍ 1 ( አንድ )

#Ethiopia | ብላቴናው ነጋሶ ጊዳዳ ሶለን ደምቢ ዶሎ ሚሲዮናውያን ትምህርት ቤት ( Missionary – School ) ገብተው እየተማሩ ሳለ አንድ ቀን ምሽት ላይ ወላጅ አባታቸው ቄስ ጊዳዳ ሶለን አንዲት አሥደንጋጭ ዜና ይዘው አመጡ።

በወርኃ ሚያዚያ – ( 1955 ዓ.ም ) “ባካችሁ ወደ ቤንች መጥታችሁ እርዱን” የምትል (ቀጭን) ደብዳቤ ደረሰው ሲኖዶሱ የነጋሶ ጊዳዳ ወላጅ አባት ቄስ ጊዳዳ ሶለን ላይ መንፈሳዊ አደራውን ይጥልባቸዋል።

ቄስ ጋዳዳ ፦ እሳቸውም ይኸን ታላቅ ሐዋርያዊ ተልዕኮን ተቀብለው መጥተው ፤በደምቢ ዶሎ ዳሩ የተደላደለ ኑሮ የጀመረውን ቤተሰባቸውን ሰብስበው ወደ ( ቤንች ማጂ ) እንደሚያቀኑ ተናገሩ።

ፀሐፊው ፦ ይኸን ያገኘውት “የጨለማ ሌላኛው ገፅታ” ከተሰኘው የነጋሶ ወላጅ አባት ግለ- ታሪክ ፅሑፍ ነው።

ነጋሶ ፦ ከወላጆቻቸው ጋር ወደ ቤንች- ሚዛን ተፈሪ ምድር ሲሄዱ ገና የ 11 ( አሥራ አንድ ) ዓመት ብላቴና ልጅ ነበሩ።

የሄድነው እናቴ፣ አባቴ፣ ታላቅ እህቴ ራሄል፣ የአክስቴ ልጅ ተስፋዬ ተፈራና ታናሽ ወንድሜ ኤልሳኢ እና እኔ ነጋሶ ነን።

ታላቅ እህታቸው ( ራሄል ጊዳዳ ) ትዳር እስክታገባ ድረስ የቤታቸው የውስጥ ዋና ረዳት ዳሩ ነበረች። ቢሆንም ነጋሶ እንደ ታላቅ ይታዩ ነበር። ውጭ የሚላላኩም ነጋሶ ነበሩ።

ይሄ ደግሞ ነጋሶ በአመዛኙም እዛው ( ጋቸብ ) ከሚገኘው ከቤንች ሕዝብ ጋር እንዲገናኙ ትልቅ እድልን ፈጠረላቸው።

ነጋሶ ፦ እዛ አከባቢ የሚናገሩት ቋንቋ “ቤንችኛ” ይባላል። በእርግጥ ከቤንች ቋንቋ በተጨማሪም እዛ ካፋ ( ካፊቾ )፣ ሸካ ( ሻኪቾ )… እነዚኸ ሁሉ በጊዜው ወደ እኛ ሚሲዮኖን ( Mission ) ጣቢያው ይመጡ ነበር።

ያረፉበት መንደር “ጋቸብ” እንደ ሆነ ነጋሶ ይናገራሉ። ጋቸብ በአከባቢው እየፏለለ እና እያጓራ የሚያልፍ የወንዝ ሥያሜ እንደ ሆነ ብላቴናው ነጋሶ ጊዳዳ ይናገራሉ።

ነጋሶ ፦ ጋቸብ መንደሮች ላይ አልፎ አልፎ ቢሆን ከርቀት ታዲያ ገላጣ ሥፍራ ይታያሉ።

ነጋሶ ፦ ታዲያ በመንደሩ ስናልፍ ጊዜ በመንገድ ይጫወቱ የነበሩ ልጆች ጠጋ ብለን “ወላጆቻችሁ የት ናችሁ” ብለን ጠየቅናቸው። “የሉም ፦ ጫካ ውስጥ ተሸሽገዋል” አሉን። በእግር አለፍን ግን ብዙም ሳንርቅ የጩኸት ድምፅ ሰማን።

ነጋሶ ፦ ጫካ የተደበቁት አባውራዎች እየተሯሯጡ ወጥተው
“ማነው ያለፈው” ይሏቸዋል ? ሕፃናት ልጆቹን።

ሕፃናቱ “አስ ኤሰርጉዌ ቄሱ ባብ ግዚዎ” ትርጓሜው (ሰው አይደለም ቄሱ አባት ነው ) ሲሉ ሕፃናቱም ይመልሳሉ።

እንግዲህ ሰው የሚሏቸው የአሥተዳደር ሰራቸኞችን እና ባለባቶችን ነው። ፍርኃታቸው እስከዚህ ድረስ ነበር።

ነጋሶ ፦ በነሱም መፍረድ አይቻልም። ( ዐፄ ኃይለ ሥላሴ ) የባርያ ንግድን እስኪያቆሙት ድረስ እንደ ከብት እየታሰሩ ተሽጠዋል። በዚ ምክንያት ቤንች ያልሆኑትን ሰዎች ይፈሩ ነበር። ይላሉ የዛኔው ነጋሶ ጊዳዳ።

ነጋሶ ፦ እናም ሚዛን-ተፈሪ እንደ ሄድኩኝ ከ 3’ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል በላይ የላቸውም። በቃ 3’ኛ (ሶስተኛ) መማርያ ክፍል ገባው። ከዚያ 2 ( ሁለት ) ዓመት አቃጠልኩኝ።

ነጋሶ ፦ ያን ጊዜ ሚሲዮኖቹ Missionaries 1 ( አንድ ) ፍልሥፍና ነበራቸው እስከ 3’ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል ድረስ ካስተማርናቸው ይበቃቸዋል። መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ ይችላሉ ይሉ ነበር።

ነጋሶ ፦ ሚሲዮኖች ( Missionaries ) እኛ እንድንማር አይፈልጉም ነበር። ሥለዚህ እኔ ተመልሼ ፤ ወደ ኦሮሚያ ደምቢ ዶሎ 3’ኛ ( ሶስተኛ ) ክፍል ልማር ዘንድ ገባው።

ነጋሶ ፦ ሚዛን- ተፈሪ የምትኖር የሚሲዬን ጣቢያው ኃላፊ ባለቤት ሚስስ ሃስፐልስ ( Miss Haspels ) ለእኔ በግል ሁሌ ከትምህርት በኃላ በልዩነት (ኦክስፍርድ- እንግሊዘኛ) ( Oxford English ) የሚባል መፅሐፍ ታስተምረኝ ነበር።

ነጋሶ ፦ በዚህ አይነት ሁኔታ መደበኛ የክፍል ትምህርቴን ሳልከታተል 2 ( ሁለት ዓመት ) ካቃጠልኩኝ በኃላ።

ነጋሶ ፦ አንድ ቀን ኳስ ሜዳ ላይ “ከበደ ጨብራሻ” ከሚባል ሰው ጋር ሜዳ ላይ በመጣላቴ ምክንያት አባቴ ቄስ ጊዳዳ ልጆቹን ይኸው ”ሥነ-ምግባር” አያሥተምርም ብለው ክፉኛ የቤተ- ክርስቲያን ሽማግሌዎች ዘንድ ከሰሷቸው።

ነጋሶ ፦ አባቴም ተናደው ከሚዛን- ተፈሪ ወደ ደምቢ ዶሎ መለሱኝ።

“ዳንዲ ፣ የነጋሶ መንገድ” ላይ ( ካነበብኩት ) የተቀነጨበ !

ጌታመሳይ ሙሉጌታ




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1