ዓለም ዋንጫ ወደ ሀገሬ መጥቷል!

- Advertisement -
Sidebar AD

— ሀገሬ ቴሌቪዥን የ2026 የዓለም ዋንጫ ባለቤት ሆነ

#​Ethiopia | የኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ተቀየረ! ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ የሚዲያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ አንድ የግል ቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም ዋንጫን በቀጥታ የማስተላለፍ ብቸኛ መብት ማግኘቱን በይፋ አስታውቋል።

​ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ በጋራ የሚዘጋጀውን የ2026 የዓለም ዋንጫ (FIFA World Cup 2026) ሀገሬ ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ በነፃ (FTA – Free To Air) በቀጥታ ያስተላልፋል።

ከሰኔ 04 እስከ ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም. የሚካሄዱትን ሁሉንም ጨዋታዎች ተመልካቾች በቤታቸው ሆነው ያያሉ።

​ ከዓለም ዋንጫ በተጨማሪ፣ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸውን የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ውድድሮች እስከ 2029 ዓ.ም. ድረስ በብቸኝነት የማስተላለፍ መብትንም ተቆጣጥሯል።

ጨዋታዎቹን በጥልቅ ትንታኔ፣ በልዩ ስፖርታዊ ዝግጅቶችና በደመቁ ስቱዲዮዎች ለማቅረብ ጣቢያው ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልጿል።

“ይህ ለሀገሬ ቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም የስፖርት ወዳጆች ትልቅ ኩራት ነው። የግል ጣቢያዎች እንዲህ ባለ ዓለም አቀፍ ደረጃ መወዳደራቸው ለኢንዱስትሪው ትልቅ መነቃቃት ነው። አሁን ኳስ ለማየት ‘ሳተላይት’ እና ‘ክፍያ’ ብሎ መጨነቅ ቀረ፤ ሀገሬ ቴሌቪዥን ዓለምን ወደ ቤታችን አምጥቶታል።”

​የስፖርት ድግሱ በሀገሬ ቴሌቪዥን ይደምቃል!

​#getu #HagerieTV #FIFAWorld Cup2026 #EthiopianMedia #SportNews #WorldCupInEthiopia #Athletics2029 #BreakingNews #ሀገሬቴሌቪዥን #ዓለምዋንጫ #ስፖርት #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1