የለንደን ማራቶን ነገ ይካሄዳል

- Advertisement -
Sidebar AD

* ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ለድል ተዘጋጅተዋል

#Ethiopia | ​ነገ ሚያዚያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም. በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ የተሰጠውና በጉጉት የሚጠበቀው የለንደን ማራቶን ይካሄዳል። የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ክብራቸውን ለማስጠበቅና አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ወደ ለንደን አምርተዋል።

በሴቶች

​ያለፈው ዓመት ሻምፒዮን እና በለንደን ማራቶን (ሴቶች ብቻ በሚሳተፉበት) የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት (2:15:50)! ትግስት ባደረገቻቸው ያለፉት 6 ማራቶኖች ከ2ኛ ደረጃ ዝቅ ብላ አታውቅም። ነገም ክብሯን እንደምታስጠብቅ ትልቅ ተስፋ ተጥሎባታል።

በወንዶች
​የኦሎምፒክና የዓለም ሻምፒዮኑ ታምራት ቶላ ለ5ኛ ጊዜ በለንደን ይሳተፋል። ከዚህ ቀደም በተሳተፈባቸው 4ቱም ውድድሮች እስከ 6ኛ ባለው ደረጃ ማጠናቀቁ ለነገው ድል ትልቅ መተማመኛ ሆኖታል።

​በ10 ሺህ ሜትር ዝነኛው ዮሚፍ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ 42 ኪሎ ሜትር (ማራቶን) የሚሮጥበት ታሪካዊ መድረክ ይሆናል። ዮሚፍ በማራቶን ምን ዓይነት አስገራሚ ውጤት ይይዝ ይሆን? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

​ያለፈው ዓመት ሻምፒዮኑ ኬንያዊው ሰባስቲያን ሳዌ፣ ዩጋንዳውያኑ ጃኮብ ኪፕሊሞ እና ጆሽዋ ቼፕቴጋይ ለኢትዮጵያውያን ብርቱ ተቀናቃኝ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

​ለንደን ማራቶን ለኢትዮጵያውያን የድል አውድማ ነው። ትግስት አሰፋ በለንደን ጎዳናዎች ላይ በድጋሚ የዓለምን ትኩረት እንደምትስብ ጥርጥር የለኝም። ዮሚፍ ቀጀልቻ ደግሞ ወደ ማራቶን ያደረገው ሽግግር ለሀገራችን አትሌቲክስ አዲስ ተስፋ ነው። ይህንን ታላቅ ውድድር በሀገሬ ቴሌቪዥን በቀጥታ መመልከት መቻላችን ደግሞ ድሉን ከቤታችን ሆነን እንድንጋራ ያደርገናል።

​ድል ለኢትዮጵያ አትሌቶች!

​#getu #LondonMarathon2026 #EthiopianAthletes #TigistAssefa #TamiratTola #YomifKejelcha #AthleticsNews #WorldRecord #HagerieTV #ለንደንማራቶን #ኢትዮጵያ #ትግስትአሰፋ #ታምራትቶላ #ዮሚፍቀጀልቻ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: