“የምወዳደረው አራዳ ወረዳ ሁለት 14 በሚባልው የምርጫ ክልል ነው” – ዲ/ን ዳንኤል ክብረት
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የማህበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሙዓዘ ጥበባት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የብልጽግና ፓርቲ እጩ ሆነው ለምርጫ መቅረባቸውን በሰጡን ቃል አረጋግጠዋል።
ለወከሉት ምርጫ ክልል ዝግጅታቸውን በተመለከተ ማብራሪያ ሲጠይቃቸው ግን “ዝርዝር ማብራሪያ ለመናገር አሁን ያለሁበት ቦታ አይመቸኝም” ሲሉ ከማብራራት ተቆጥበዋል።
የብልጽግና ፓርቲ እጩ ሆነው ቀርበዋል መባሉ ግን እውነት ነው? በሚል ላቀረብነው ጥያቄ ግን፣ “አዎ” የሚል አጭር የማረጋገጫ ምላሽ ሰጥተውናል።
የትኛውን አካባቢ ወክለው ነው ታዲያ የሚወዳደሩት? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ፣ “የምወዳደረው አራዳ ወረዳ ሁለት 14 በሚባልው የምርጫ ክልል ነው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በ6ኛው ዙር ጠቅላላ ምርጫ በግላቸው በመወዳደር የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባል መሆናቸው ይታወሳል። በሰባተኛው ምርጫ ደግሞ የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነዋል።
@seledadotio

No comments yet.