#Ethiopia | የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብን ከገባበት የፋይናንስ ቀውስና ከፊፋ የዝውውር እገዳ ለማውጣት፣ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ የ26 ሚሊየን ብር ተጨማሪ ድጋፍ አደረጉ።
አቶ ጀማል ባለፈው ወር ሚድሮክ ከሰጠው 50 ሚሊየን ብር በተጨማሪ፣ ሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. 26 ሚሊየን ብር ለክለቡ ገቢ አድርገዋል።
ለምን ዋለ? ይህ ገንዘብ በቀጥታ የውጭ ተጫዋቾችን ደመወዝ፣ ወለድ እና የቅጣት ክፍያዎችን ለመሸፈን የሚውል ነው።
ክፍያው በመፈጸሙ ምክንያት በፊፋ ተጥሎ የነበረው አዲስ ተጫዋቾችን የማስፈረም እገዳ የሚነሳ ይሆናል።
እገዳው መነሳቱን ተከትሎ፣ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ስጋት ላይ የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ለቀሪው የውድድር ዘመንና ለሚቀጥለው ዓመት አዳዲስ ተጫዋቾችን በይፋ መመዝገብና ማጠናከር ይችላል።
ክለቡ ለአቶ ጀማል አህመድና ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ያለውን የከበረ ምስጋና በራሱና በደጋፊዎቹ ስም አቅርቧል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
#StGeorgeSA #KidusGiorgis #EthiopianPremier League #MidrocInvestmentGroup #JemalAhmed #Feresegnoch
Source: GetuTemesgen








No comments yet.