#Ethiopia | የመድፈኞቹ አለቃ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው ባስመዘገበው ውጤት ደስተኛ ቢሆኑም፣ ስብስባቸው ፍጹም ለመሆን ግን ገና መስተካከል ያለባቸው “የቤት ስራዎች” እንዳሉበት በግልጽ ተናግረዋል።
አሰልጣኙ ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በሰጡት አስተያየት የቡድናቸውን ጥንካሬ እና ድክመት እንዲህ አብራርተዋል፦
ተጫዋቾቻቸው በሜዳ ላይ ያሳዩት ስነ-ምግባር እና ሳይፈሩ ለመጫወት ያደረጉት ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
ከጨዋታው የሚፈለገውን ሶስት ነጥብ ይዞ መውጣት መቻላቸው ትልቅ ስኬት መሆኑን አምነዋል።
አርቴታ ለድሉ እውቅና ቢሰጡም፣ ቀጣይ ስራዎቻቸው ላይ ግን ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡
ቡድኑ የሚያገኛቸውን ወርቃማ የጎል እድሎች በአግባቡ መጠቀም ላይ ክፍተት እንዳለበት ጠቁመዋል።
ኳስ በጠፋባቸው ወቅት በፍጥነት ተጭኖ በመንጠቅ ረገድ ከዚህ የተሻለ መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ተቃራኒ ቡድን ወደ ማጥቃት በሚሸጋገርበት ወቅት የሚሰነዝራቸውን ጥቃቶች ቀድሞ በማቋረጥ ረገድ መሻሻል እንደሚፈልጉ ተናግረዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
Source: GetuTemesgen









No comments yet.