አቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ 16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አከበረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ “የቴክኖሎጂ ልህቀት ለሀገር ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል 16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት በፓናል ውይይት፣ በቴክኖሎጂ ኤግዚቢሽንና በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት አክብሯል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የፓናል ውይይት የተካሔደ ሲሆን፣ የቴክኒክና ሙያ ስትራቴጂዎች እና ለውጦች፣ የኢትዮጵያ ቴክኒክና ሙያ አሰራሮች፣ የተገኙ ወጤቶችና ተግዳሮቶች፣ የኢንተርፕራይዞችና ቴክኖሎጂዎች ፋይዳን የተመለከቱ የውይይት መነሻ ፅሑፎች በምሁራን ቀርበዋል።

ውይይቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትን ከገበያ ፍላጎት ጋር ማስማማት፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመፍጠር ወደ ማህበረሰቡ ለገበያ ማውረድ እንዲሁም የህዝብና የግል ተቋማት ትብብርን ማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑን የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዋና ዲን አቶ ፀጋዬ አዱኛ ገልፀዋል።

ከደረጃ 01 እስከ ደረጃ 05 በተለያዩ ዲፓርትመንቶች 3609 ሰልጣኞችን እያሰለጠን ነው ያሉት አቶ ፀጋዬ ዓለማቀፍ ስታንዳርድን ለማሟላትና የስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ ባደረግነው ርብርብ የISO 9001፡2015 እውቅና አግኝተናል ያሉ ሲሆን በ2018 ዓ.ም 22 አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች በሰልጣኞች እና በአሰልጣኞች መሰራታቸውን ተናግረዋል።

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የውጤት ተኮርና ተቋማት ልማት ኃላፊ ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ እንደገለጹት ፣በየዓመቱ የሚከበረው የቴክኒክና ሙያ ሳምንቱ ወጣቶች በተግባር ላይ የተመሠረተ ሥልጠና እንዲያገኙ፣ የሥራ ዕድሎችን እንዲያስሱና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎችን በቀጥታ እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ብለዋል።

ወ/ሮ ዳግማዊት አክለውም፣ የፓናል ውይይቱ ደግሞ ተኪ ምርቶችን በማምረት ከትምህርት ተቋማት እስከ ሥራ ቦታ ድረስ ያለውን የክህሎት ክፍተት ለመሙላት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ሥራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚደክሳ ከበደ በበኩላቸው፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ወደ ሥልጠና መርሃ ግብር ማስገባት የሚቻልባቸው እድሎች እንዳሉ የተናገሩ ሲሆን፣ሳምንቱ ተማሪዎች በተግባር ላይ የተመሰረተ ክህሎት እንዲያጎለብቱ፣ ከኢንዱስትሪው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት እንዲፈጥሩና የራሳቸውን ውጤት በኤግዚቢሽን እንዲያሳዩ ልዩ ዕድል እንደፈጠረላቸውም ገልፀዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)

#getutemesgen #getu #ጌጡ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1