የሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ድርና ማግ ሆነናል አሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የሩሲያው መከላከያ ሚኒስትር አንድሬ ቤሎሶቭ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ የሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብር ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቀዋል።

ይህ ጉብኝት በቃላት ደረጃ ከሚገለጽ ዲፕሎማሲ ባለፈ፣ በተግባር የሚታይ ስልታዊ ዝግጅት የታየበት ነው።

​ሁለቱ ሀገራት ከ2027 እስከ 2031 የሚዘልቅ የጋራ ወታደራዊ ግንኙነት ፍኖተ ካርታ ላይ ተስማምተዋል። ይህም ትብብራቸው ለረጅም ጊዜ የሚቆይ መሆኑን ያሳያል።

​በሰኔ 2024 የተፈረመው ስምምነት አንዱ ሀገር ጥቃት ቢሰነዘርበት ሌላኛው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲያደርግ ያስገድዳል። ይህም ሰሜን ኮሪያን የሩሲያ ቀጥተኛ የጦር አጋር አድርጓታል።

​ቤሎሶቭ ሰሜን ኮሪያ በዩክሬን ጦርነት ወቅት ለሩሲያ ላሳየችው “ወንድማዊ ድጋፍ” እና በኩርስክ ክልል ለተሳተፉት የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና ሰጥተዋል።

​ይህ ጥምረት በ”እጅ በእጅ” ግብይት ላይ የተመሰረተ ይመስላል። ምዕራባውያን እንደሚሉት ከሆነ፦

ወደ 14,000 የሚጠጉ ወታደሮችን እና የጦር መሣሪያዎችን ለሩሲያ ግንባር አሰልፋለች።

​ሩሲያ ምን ትሰጣለች? በምላሹ ዘመናዊ የወታደራዊ ቴክኖሎጂ ድጋፍ፣ የምግብ ዋስትና እና የኃይል (ኢነርጂ) አቅርቦትን ለሰሜን ኮሪያ ታረጋግጣለች።

ይህ ጥምረት በምዕራባውያን ዘንድ ከፍተኛ ስጋት የፈጠረው ሰሜን ኮሪያ በምትገኝበት ቀጠና (ምስራቅ እስያ) ያለውን የኃይል ሚዛን ሊያናጋ ስለሚችል እና የዩክሬን ጦርነትን መልክ ሊቀይር ስለሚችል ነው።

የሩሲያ ቴክኖሎጂ እና የሰሜን ኮሪያ የሰው ኃይል መቀላቀል ለኔቶ (NATO) አባላት ቀላል የማይባል የቤት ስራ ሆኖባቸዋል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#ሩሲያ #ሰሜንኮሪያ #ወታደራዊትብብር #ኪምጆንግኡን #አንድሬቤሎሶቭ #የዓለምፖለቲካ #ዩክሬን #ዜና


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1