ጅማ ደምቃ አረፈደች!

- Advertisement -
Sidebar AD

ታላቁ ሩጫ በጅማ በድምቀት ተከናወነ!

#Ethiopia | የ”ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ” የሩጫ ተከታታይ ውድድር አካል የሆነው የ2018ቱ የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ ዛሬ ጠዋት በጅማ ከተማ በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። በውድድሩ ላይ ከ4,000 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች እና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ስፖርት አፍቃሪዎች ተሳትፈዋል።

​የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ከድር እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች በክብር እንግድነት ያስጀመሩት ይህ ውድድር፣ “ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ” (End Polio Now) በሚል መሪ ቃል የጤና ግንዛቤን በስፋት ያስተጋባ መድረክ ነበር።

​🏆 የውድድሩ አሸናፊዎች፦

​የ15 ኪ.ሜ የጤና ሯጮች ከአባ ጅፋር ቤተመንግስት ተነስተው በከተማው መሃል ፈረንጅ አራዳ በተጠናቀቀው ውድድር፤ በወንዶች ጃፈር ጀማል፣ በሴቶች ደግሞ የግሌ እሸቱ ቀዳሚ በመሆን አሸንፈዋል።

እጅግ አስደሳችና ተቀራራቢ ፉክክር በታየበት
የ5 ኪ.ሜ የፕሮፌሽናል አትሌቶች ፉክክር
፤ በወንዶች ብሩክ ዘለቀ፣ ኦሊፈን ዲባባ እና ማዲ ሪዳ ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዘዋል። በሴቶች ዝናሽ ግዛው አንደኛ ስትወጣ፣ ማርሸት መላኩ እና ሊና አብዱ ተከታትለው ገብተዋል።

​ከዋናው ውድድር በተጨማሪ ዕድሜያቸው ከ16 እና ከ11 ዓመት በታች ለሆኑ ታዳጊ ህፃናት የተዘጋጀው መርሐ-ግብር፤ የወደፊት ኢትዮጵያውያን ተተኪ ኮከብ አትሌቶችን አቅም ያሳየ ሲሆን፣ አሸናፊዎችም ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ተበርክቶላቸዋል።

​በቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም በሌሎች አጋር ድርጅቶች ደጋፊነት የተሳካው የጅማው መድረክ፤ የዘንድሮው ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ መዳረሻ ነው። ቀጣዩ መድረክ በሯጮች መፍለቂያዋ ቦቆጂ ከተማ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል።

ለ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ

ያፌት ገ/ህይወት
ከጅማ ዞን ፤ ጅማ ከተማ






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2