#Ethiopia | የማሊ የመከላከያ ሚኒስትር ሳዲዮ ካማራ በታጠቁ ሀይሎች የተቀናጀ ጥቃት ተገደሉ።
ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ በመላ አገሪቱ ባሉ ወታደራዊ ቦታዎች ላይ በተፈፀሙ የተቀናጁ ጥቃቶች መገደላቸውን የመንግስት ቃል አቀባይ አረጋግጠዋል።
ሚኒስትሩ ህይወታቸው ያለፈው የታጠቁ ሀይሎች በቤታቸው ላይ በከፈቱት ጥቃት መሆኑን ቃል አቀባዩ ኢሳ ኦስማን ኩሊባሊ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።
በካቲ የጦር ሰፈር የሚገኘው የካማራ መኖሪያ ቤት በእለተ ቅዳሜ በአልቃይዳ እና በቱዋሬግ አማፂያን የጋራ ትብብር በተመሳሳይ ሰዓት ያልጠበቀው ጥቃት እንደተከፈተበት መረጃዎች ጠቁመዋል።
ጄኔራል ሳዲዮ ካማራ በ 2020 እና በ 2021 በተከታታይ በተካሄዱት የማሊ መፈንቅለ መንግስት ውስጥ አልፎ ስልጣን የያዘው የሀገሪቱ ወታደራዊ መንግስት ቁልፍ ሰው ነበሩ።
እንደ አልጀዚራ ዘገባ ሚኒስትሩ በወታደራዊ መንግስት ውስጥ ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው ሲሆን የወደፊቱ የማሊ መሪ ሊሆኑ እንደሚችሉ ግምቶች ይሰነዘሩ ነበር።
ካማራ ከሀገሪቱ ጊዜያዊ መሪ አሲሚ ጎይታ ከሚኖሩባት ባማኮ 15 ኪሎ ሜትሮችን ርቀው ጠንካራ ምሽግ ባላት ካቲ ይኖሩ የነበረ ሲሆን ጥቃቱ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ስለመሆኑም ተረጋግጧል።
በሌላ በኩል የካማራ ሁለተኛ ሚስት እና ሁለት የልጅ ልጆቹም በቤቱ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ተገድለዋል ሲል የኤኤፍፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።
የአፍሪካ ህብረት፣ የእስልምና ትብብር ድርጅት ዋና ፀሐፊ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ቢሮ እና የአውሮፓ ህብረት ጥቃቶቹን አውግዘዋል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #NBC
Source: GetuTemesgen









No comments yet.