” የኢራን ሕዝብ ለሉዓላዊነቱ በድፍረት እና በጀግንነት እየተፋለመ ነው ” – ፑቲን

- Advertisement -
Sidebar AD

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከኢራኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ጋር በሴንት ፒተርስበርግ ተገናኝተው ተወያትተዋል፡፡

ውይይቱ ​የተነሱ ዋና ዋና ነጥቦች ፑቲን፣ ከኢራኑ የሉዓላዊ መሪ መልዕክት እንደደረሳቸው ገልጸዋል።

ሩሲያ፣ የኢራን ሕዝብ ይህንን የፈተና ወቅት እንደሚወጣው እና ሰላም እንደሚመጣ ተስፋ ታደርጋለች ሲሉ ፕሬዝዳንቱ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ሩሲያ ለኢራንና ለሌሎች የቀጣናው ሀገራት ጥቅም ሲባል በመካከለኛው ምስራቅ በተቻለ ፍጥነት ሰላም እንዲመጣ የሚቻላትን ሁሉ እንደምታደርግ ቭላድሚር ፑቲን ገልጸዋል።

ፑቲን ለሉዓላዊ መሪው ሞጅታባ ካሜኒ ጤና መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢራን ሕዝብ ባሳየው ቆራጥነት የአሜሪካን የወረራ ጥቃት መቋቋም መቻሉን እና ለወደፊትም እንደሚጸና አራግቺ ተናግረዋል።

የኢራኑ የሉዓላዊ መሪ ሞጅታባ ካሜኒ እና ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ለፑቲን መልካም ምኞታቸውን አስተላልፈዋል ሲል ስፑትኒክ ዘግቧል።


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1