የወጣቱን እስጢፋኖስ አምሃን ሕይወት እንታደግ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​የ17 ዓመቱ ወጣትና የ11ኛ ክፍል ተማሪው እስጢፋኖስ አምሃ፣ በደም ካንሰር (Leukemia) ህመም ምክንያት በከባድ ፈተና ውስጥ ይገኛል።

ለ6 ወራት በኬሞቴራፒ ታክሞ ወደ ጤናው ተመልሶ የነበረ ቢሆንም፣ በሽታው በድጋሜ በማገርሸቱ በአስቸኳይ ወደ ውጭ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት ሐኪሞች አዝዘዋል።

​የህክምና ወጪ
ለህክምናው ከ7 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልጋል። ይህ መጠን ለቤተሰቡ ከአቅም በላይ በመሆኑ የእናንተን የደጋግ ወገኖቹን እገዛ ይፈልጋል።

​እናቱ ዝናሽ ተፈራ እንዲህ ይላሉ
“የልጄን ህይወት ለመታደግ የእናንተን እገዛ እፈልጋለሁ… በሃገር ውስጥም ሆነ በውጪ ሀገር የምትገኙ ደጋግ ወገኖቼ በቻላችሁት ሁሉ እንድታግዙኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃችኋለሁ።”

​ ድጋፍ ለማድረግ፦

​የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፦ 1000760949918

​GoFundMe: https://gofund.me/47505f930

​ለተጨማሪ መረጃ፦
0968 881906
0930 288790
0923 669504
0911 158119

ወገኖቼ፣
ዛሬ የቡና ደጋፊዎች ደም በመለገስና ዮሚፍ ለንደን ላይ ታሪክ በመስራት ያስደሰቱን ቀን ነው። ይህንን ደስታችንን ሙሉ የምናደርገው ደግሞ እንደ እስጢፋኖስ ያሉ ተስፋ ያላቸው ወጣቶችን ከሞት አፋፍ ስንታደግ ነው።

7 ሚሊዮን ብር ለቤተሰቡ ትልቅ ቢሆንም፣ ለእኛ ለኢትዮጵያውያን ግን ተባብረን የማናሸንፈው ቁጥር አይደለም።

እባካችሁ በጸሎትም በገንዘብም ከጎኑ እንቁም!”

​አንድ ሰው ለብዙዎች፣ ብዙዎች ለአንድ ሰው!

​#getu #SaveEstifanos #HelpEstifanos #LeukemiaAwareness #EthiopianHumanity #EmergencyAppeal #HealthcareEthiopia #ድረሱልን #እስጢፋኖስአምሃ #ሰብአዊነት #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: