#FastMereja I በገርጂ ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ለሦስት ዓመታት በቆየው የአስተዳደር ዘመናቸው የነበረውን መቃቃር በማስወገድ ሰላምና ልማትን ላሰፈኑት መላከ ፀሐይ በቀለ ተሰማ የኤሌክትሪክ መኪና ሽልማት ተበረከተላቸው።
የደብሩ ካህናት፣ የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶችና የሰበካ ጉባኤው በጋራ በመሆን ያዘጋጁት ይህ የዕውቅና ፕሮግራም፤ መላከ ፀሐይ በቀለ በካቴድራሉ የነበረውን የውስጥ ሽኩቻ በማስወገድ፣ የስብከተ ወንጌል አገልግሎትን በማጠናከርና የልማት ሥራዎችን በማስፋፋታቸው የBYD E2 የኤሌክትሪክ መኪና ቁልፍ በብፁዓን አባቶች እጅ ተረክበዋል።
አስተዳዳሪው በሽልማቱ ወቅት በደስታ እንባ እየታነቁ ባደረጉት ንግግር፤ “እኔ ያደኩት በዚህ ደብር ነው፤ ከእናንተ የተለየ ብቃት ኖሮኝ ሳይሆን ሰማዕቱን ለማገልገል በመመረጤ ነው” በማለት ለምዕመናኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በዕለቱ የተገኙት ብፁዕ አቡነ መቃሬዎስ በሰጡት ቃለ ምዕዳን፤ ሌሎች የደብር አስተዳዳሪዎችም ቢሮ ዘግቶ ከመቀመጥ ይልቅ እንደ መላከ ፀሐይ በቀለ ዝቅ ብለው በመሥራትና ሰላምን በማስፈን ከአባቱ ሊማሩ እንደሚገባ አሳስበዋል።
Source: FastMereja









No comments yet.