ድምጻዊ አስገኛው አሽኮ (አስጌ ዴንዳሾ) በሴቶች ላይ የሰነዘረው አስተያየት በማህበራዊ ሚዲያ መነጋገሪያ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I​ ታዋቂው ድምጻዊ አስገኛው አሽኮ (አስጌ) የሴቶችን የማመዛዘን ብቃትና ትኩረት አስመልክቶ በማህበራዊ ገጹ ያሰፈረው አነጋጋሪ መልዕክት በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ ክርክር ቀስቅሷል።

​ድምጻዊው ባስተላለፈው መልዕክት፤ “የሴት ልጅ አዕምሮ ከጭንቅላት ቦታውን ስቶ ኪስ፣ መልክ እና ዳሌ ስር ከተወሸቀ መቼም አያዝንም፣ አያመዛዝንም” ሲል የሰነዘረ ሲሆን፣ ይህም በሴቶች ስነ-ልቦና እና በቁሳቁስ ፍላጎት ዙሪያ ያለውን ምልከታ የነካ ሆኗል።

​አስጌ ይህንኑ መልዕክት ተከትሎ “እቺንማ ወርደን እንነጋገር” በማለት ተከታታዮቹን ለውይይት የጋበዘ ሲሆን፣ በሰነዘረው ሃሳብ ዙሪያ በተለይ በሴት ተከታታዮቹ ዘንድ የተደበላለቁ አስተያየቶች እየተሰነዘሩበት ይገኛል። አንዳንዶች ሃሳቡን ተራ ትችት በማለት እየተከራከሩ ይገኛሉ።


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1