#ጭርት የሚባለው የቆዳ በሽታ (#tineacorporis) ሕክምናው ምንድን ነው
ጭርት ማለት ደርማቶፋይትስ በሚባሉ የፈንገስ ዝርያዎች አማካኝነት የሚመጣ የላይኛውን የቆዳ ክፍል የሚያጠቃ የቆዳ በሽታ ሲሆን ህፃናትን ጨምሮ በሁሉም የእድሜ ክልል ሊከሰት የሚቺል ተላላፊ በሽታ ነው።
መተላለፍያ መንገዱ ምንድነው?
ህፃናት ይህንን የቆዳ በሺታ በበሽታው ከተያዙ ልጆች አዋቂ ሰዎች ወይም ከእንስሳት ሊተላለፍባቸው ይችላል።
በተለይ ደሞ ህፃናት ላይ የሚተላለፈው በፎጣ አልጋ ልብስ ካልሲ የፀጉር ማበጠሪያ በጋራ መጠቀም እና ንክኪ መፍጠር ዋነኛ መተላለፊያ መንገዶች ናቸው።
ምልክቶቹስ ምንድናቸው
በሰውነት ላይ ክብ ክብ የሆነ ፣ ጠርዝ ጠርዙ ቀላ እና ከፍ ያለ ይሆናል
የማሳከክ ስሜት ሊኖረውም ላይኖረውም ይቺላል እየሰፋ ከሄደ ነጭ እንደ ቅርፊት ያለ ነገር ሊወጣ ይችላል።
ጭርት በሽታ መሆኑን እና አለመሆኑ በምን ይታወቃል
አንድ የቆዳ በሽታ ጭርት መሆኑን እና አለመሆኑን በህክምና ባለሙያው በቆዳ ላይ የወጣውን ነገር አይቶ እንደ አስፈላጊነቱ ከቆዳ ላይ ናሙና በመውሰድ በላቦራቶሪ በመመርመር ፈንገስ መኖር እና አለመኖሩን ማወቅ ይችላል።
ካልታከመ የሚያመጣውስ ችግር አለ ይሆን?
የሚያሳክክ፣ የተቆጣ እና የቆዳ መሰንጠቅ ሲኖር ለሌላ ባክቴሪያ ኢንፌክሽን (secondary bacterial infection) ሊጋለጡ ይችላሉ።
ኅይለኛ የቆዳ መቆጣት/ብግነት
መከላከል ይቻላል
የሚከተሉን ጥንቃቄዎችን በማድረግ የህፃናትን የጭርት በሺታ መከላከል ይቻላል
✔️ የህፃናት ግል እና የአካባቢ ንፅህናን መጠበቅ
✔️ ህፃናትን ሰውነታቸውን ካጠብን በዋላ በንፁህ ፎጣ ወይም ጨርቅ በደንብ ማድረቅ
✔️ ህፃናት በግል መጠቀም ያለባቸውን ነገሮች በጋራ አለመጠቀም ለምሳሌ ፎጣ የዉስጥ ልብሶች ካልሲ እና የመሳሰሉት
✔️ በተቻለ መጠን በዚህ በሽታ ካለባቸው ሌሎች ህፃናት ጋር ንክኪ አለመፍጠር
✔️ በአካባቢያችን የታመሙም እንስሳት ካሉ የእንስሳት ሀኪም ጋር በመውሰድ እና ማሳከም ተገቢ ነው።
ህክምናውስ ምንድነው
መድሃኒቱ እንደ በሺታው ስፋት እና ጥልቀት የሚወሰን ሲሆን በቦታው ላይ የሚቀባ ቅባት ወይም የሚዋጥ መድሃኒት ሊድን ይችላል ።
@seledadotio

No comments yet.