በአዲስ አበባ ከተማ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ4 ሺህ በላይ የፍቺ ምዝገባ መከናወኑ ተነገረ
የሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት በዘጠኝ ወራት ውስጥ በወቅታዊ፣ በዘገየ፣ጊዜ ገደቡ ባለፈ ልደት 324,363 የጋብቻ 28,604፣ የሞት 19,448፣ የጉዲፈቻ 278 በአጠቃላይ የአምስቱም ኩነቶች 382ሺ309 አፈፃፀም ምዝገባ ማድረጉን አስታውቋል ፡፡
በተጨማሪም በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 4452 ወቅታዊ የፍቺ ምዝገባ ተደርጓል ። ከጤና ተቋማት በሚመጣ የማሳወቂያ ወረቀት የተመዘገበ የልደት እና የሞት 78.04% ምዝገባ በማድረግ የዕቅዱን 84.63% ለማከናወን መቻሉን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በሌላ በኩል 142,159 ያላገባ ማስረጃ አገልግሎት የተሰጠ ሲሆን 600,589 ነዋሪዎችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመመዝገብ አገልግሎት መስጠት ተችሏል። ከተሰጠው የነዋሪነት መታወቂያ ውስጥ ዲጂታል 99.78%፣ ማኑዋል 0.22% ማድረስ መቻሉ ነው የተገለጸው፡፡
በመጨረሻም የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ንጉሴ በበጀት ዓመቱ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ያስመዘገባቸውን ውጤቶች እና የነበሩትን ጥንካሬዎች በመያዝ በቀጣይ የመጨረሻ ሩብ ዓመት ውስጥ በዕቅድ ተይዘው ያላለቁ ሥራዎችን የሚያጠናቅቅበት እና ተቋሙ ከማዕከል እስከ ወረዳ ባለው አደረጃጀት የሚገኙ አመራሮች እና ባለሙያዎች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው በመስራት የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
@seledadotio

- Advertisement -

No comments yet.