“እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ”

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

የራማው ልዑል፣ መጋቤ ሐዲስ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል በሉቃስ 1÷19 ብሎ መገኛ ስፍራውንና እግዚአብሔር የሰጠውን ክብር በይፋ ያወጀ መልአክ ነው፡፡ ገብርኤል ማለት የእግዚአብሔር ኃይል ነው ማለት ነው። ቅዱስ ገብርኤል ድንቅ መልእክቶችን በማድረስና የተረበሹትን በማረጋጋት ይታወቃል፡፡ ነገደ መላክት በሰማይ አምላካቸው ተሰውሮባቸው ማን ፈጠረን ብለው በተጨነቁ ጊዜ ያረጋጋቸው እርሱ ነው፡፡ በክብሩ ከፍ ብሎ በመፈጠሩ መላዕክትን እኔ ነኝ የፈጠርኳችሁ ብሎ ሊያስት የሞከረውን የሀሰት አባት የያኔው (ሳጥናኤል) ጠላት ዲያብሎስ ተከራክሮ የረታው እርሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡

መላእክት የሰው ልጆች አፍቃሪና ወዳጅ ናቸው፡፡ ከእነዚህ አንዱ የአምላክና የሰው ልጆች ወዳጅ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ይህንም ህጻኑ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣን ከእሳት ሲያድን አይተነዋል፡፡ ዳግመኛም የፋርስ ንጉሥ የነበረው ናቡከደነፆር እግዚአብሔር አምላክ ምድሪቱንና ሕዝቡን እንዲያስተዳድር ቢፈቅድለት በትዕቢት ተሞላ፡፡ በዳንኤል 3፥1 እንደተጻፈው “ሁሉን በኃይሌ አደርጋለሁ፣ በማስተዋል ጥበቤም የአሕዛብን ድንበሮች አርቃለሁ፣ ሀብታቸውንም እዘርፋለሁ፣ የሚቀመጡባቸውንም ከተሞች አናውጣለሁ፣ በእጄም ዓለምን ሁሉ እንደ ወፍ ቤት እሰበስባለሁ፣ እንደ ተተወ እንቁላልም እወስዳቸዋለሁ፤ ከእኔም የሚያመልጥ የለም፤ የሚቃወመኝም የለም” በሚል ትዕቢት ቁመቱ ስድሳ ክንድ፣ ወርዱም ስድስት ክንድ የወርቅ ጣዖትን አሠርቶ በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ ያልሰገደለት እንዲገደል አዋጅ አስነገረ፡፡

አናንያ፣ አዛርያ፣ ሚሳኤል የተባሉ ሦስት ሕጻናት በንጉሡ ፊት ቆመው “ንጉሥ ሆይ እኛ የምናመልከው አምላክ በሰማይ አለ፡፡ ከሚነድደው ከእቶኑ እሳት ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ንጉሥ ሆይ! ይህም ባይሆን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድ ዕወቅ” ባሉ ጊዜ ወደ እቶን እሳት ሲጣሉ ደርሶ ያዳናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው፡፡ ናቡከደነጾርም ተገርሞ እነሆ ሰሦስት ሰዎ በእሳቱ ላይ ጥለን ነበር እኔ ግን አራት ሰዎች አያለሁ፣ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን መልክ ይመስላል አለ፡፡ ቅዱስ ገብርኤል የአምላክ ባለሟል ነው፡፡ ለካሕኑ ለቅዱስ ዘካርያስ እንደነገረው በእግዚአብሔር ፊት መቆሙ ታላቅ ባለሟል መሆኑን የሚያሳይ ነውና፡፡

ገዳማውያን እናቶችና አባቶቻችን ሊቀ መላአኩ በእግዚአብሔር ፊት በቆመ ጊዜ እንዲያማልዳቸው በዘወትር በጸሎታቸው ተግተው ይጠሩታል፡፡ ከበረከታቸው እንድንካፈል ገዳማቸውን እንደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2