የቴክኖሎጂው ጦርነት ጋለ! ቻይና የአሜሪካን የAI ምስጢሮች ሰርቃለች ተባለ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​ዋይት ሀውስ (White House) በይፋ ባወጣው መግለጫ፣ ቻይና እጅግ ዘመናዊ የሆኑ የአሜሪካን የAI ቴክኖሎጂ ምስጢሮችን በመስረቅ የራሷን AI ገንብታለች ሲል ከሰሰ። ይህ ድርጊት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ጥሎታል።

​ ድርጊቱ እንዴት ተፈጸመ?
(The “Distillation” Method)

​በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ የሀሰት አካውንቶችን በመጠቀም ወደ አሜሪካ የAI ሲስተሞች ዘልቀው በመግባት መረጃዎችን ቀድተዋል።

​የቴክኖሎጂ ስርቆት (Distillation)
ሌላው ሰው ለፍቶ የሰራውን የቤት ስራ ኮርጆ እንደራስ አድርጎ እንደማቅረብ ማለት ነው። ቻይና የአሜሪካን ምርጥ የAI ክፍሎች በመቅዳት ያለምንም ወጪ የራሷን ቴክኖሎጂ ገንብታለች ተብሏል።

​የአሜሪካ መንግስት በዚህ ድርጊት እጅግ መቆጣቱን የገለጸ ሲሆን፣ ቻይና ግን ክሱን “መሰረተ ቢስ” ስትል አጣጥላለች።

​ የትራምፕና የፕሬዝዳንት ዢ መገናኘት

የሚቀጥለው ወር ዶናልድ ትራምፕ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ዢ ጂንፒንግ ጋር የሚያደርጉት ስብሰባ፣ በዚህ አዲስ የስርቆት ክስ ምክንያት እጅግ አሳሳቢና “Awkward” እንደሚሆን ይጠበቃል።

​ ዛሬ ዓለም በጉልበት ብቻ ሳይሆን በቴክኖሎጂም እየተፋለመች ነው። AI የወደፊቱ ዓለም ቁልፍ በመሆኑ፣ እንዲህ ያሉ የስርቆት ክሶች የሀገራትን ደህንነት አደጋ ላይ ይጥላሉ።

ቴክኖሎጂው ለበጎ ነገር ከመዋል ይልቅ ለስለላና ለስርቆት መዋሉ ያሳስባል። ትራምፕ በሚቀጥለው ወር ለሚያደርጉት ጉብኝት ይህ ክስ ትልቅ ራስ ምታት እንደሚሆንባቸው ግልጽ ነው!

​የቴክኖሎጂው ጦርነት ወዴት ያመራ ይሆን?

​#getu #TechWar #USvsChina #AISecrets #ArtificialIntelligence #TrumpXiMeeting #CyberSecurity #GlobalNews #ቴክኖሎጂ #አርቴፊሻልኢንተለጀንስ #አሜሪካናቻይና #ሰበርመረጃ #ጌጡተመስገን #GetuTemesgen


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: