ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ ድምጹም እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ

- Advertisement -
Sidebar AD

🙏

ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ለነቢዩ ዳንኤል ማስተዋልንና ጥበብን የሰጠ፣ እግዚአብሔር አምላክ የሰው ልጆችን ከሰይጣንና ከሞት ባርነት ነጻ ሊያወጣቸው ሰው እንደሚሆን ሰማይንና ምድርን አሳልፎ በቅዱሳን ላይ ነግሦ እንደሚኖር በምሳሌ ገልጾ ያስተማረው መልአክ ነው፡፡ ነቢዩም የቅዱስ ገብርኤልን አስፈሪ ግርማ ሲገልጽ “ዐይኖቼንም አነሣሁ “እነሆም በፍታ የለበሰውን ጥሩም የአፌዝን ወርቅ በወገቡ ላይ የታጠቀውን ሰው አየሁ፡፡ አካሉም እንደ ቢረሌ ይመስል ነበር፤ ፊቱም እንደ መብረቅ አምሳያ ነበረ፤ ዐይኖቹም እንደሚንበለበል ፋና፣ ክንዶቹና እግሮቹም እንደ ጋለ ናስ፣ የቃሉም ድምፅ እንደ ብዙ ሕዝብ ድምፅ ነበረ፡፡ ይህንም ታላቅ ራእይ አየሁ፤ ኀይልም አልቀረልኝም፤ ክብሬም ወደ ውርደት ተለወጠብኝ ኀይልም አጣሁ፡፡ የቃሉንም ድምፅ ሰማሁ፤ የቃሉን ድምፅ በሰማሁ ጊዜ ደንግጬ በምደር ላይ በግምባሬ ተደፋሁ” አለ፡፡

ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ሰውና አምላክ ማለት ሲሆን ከዋነኞቹ የመላዕክት አለቆች አንዱ ሲሆን አርባብ፣ አጋእዝት ወይም ጌቶች የተባሉትን ነገድ የሚመራ ነው፡፡ ከበታቹም የሚመራቸው ዐሥር ነገደ መላእክት አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክት በቅዱስ ሚካኤል ፊት አውራሪነት የሰው ልጆች ጠላት ዲያብሎስን ተዋግተው ድል ከመንሳታቸው አስቀድሞ እግዚአብሔር መላዕክት ፈጥሮ ተሰወረባቸው፡፡ ይህን ጊዜ ማን ፈጠረን ብለው ግራ ሲጋቡ የመላዕክት አለቃ አድርጎ የፈጠረው ሳጥናኤል እኔ ፈጠርኳችሁ አላቸው፡፡ አንዳንዶች አመኑት፣ አንዳንዶችም ግራ ተጋብተው መወሰን አልቻሉም፡፡ ሊቀ መላዕክት ቅዱስ ገብርኤል ግን ሳጥናኤልን “አንተ ፈጣሪ ከሆንክ ደግመህ ፈጥረህ አሳየን አለው፡፡ ሳጥናኤልም ቢሞክር አቃተው፡፡ ይህን ጊዜ ቅዱስ ገብርኤል ሳጥናኤልን በመቃወም “አይዞአችሁ ፈጣሪያችን ፈጥሮ አይጥለንምና እስክናውቀው ድረስ በያለንበት እንቁም፡፡” በማለት መላእክትን አረጋጋቸው፡፡

በራእይ 18÷1 “ከዚህ በኋላ ታላቅ ሥልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፤ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች፡፡” ተብሎ እንደተጻፈ ቅዱስ ገብርኤል ብርሃናዊ መልአክ ነው፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊትም በመዝሙር 103÷4 “መላእክቱን የእሳት ነበልባል የሚያደርግ” እንዳለው ቅዱስ ገብርኤል ነበልባላዊ መልአክ ነው፡፡ ነቢዩ ሔኖክም 10÷14 “በሠራዊት ሁሉ ላይ የተሾመ መልአክ ቅዱስ ገብርኤል ነው” ይላል፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችም የቅዱስ ገብርኤልን ቁጣ የምንሰማና የምናይ ሲሆን ለምሳሌ ካህኑ ዘካርያስ የመልአኩን ብስራት ባለመቀበሉ ዲዳ ሁኗል፡፡ ዛሬም ይህን አማላጅነቱንና ፈጣን ተራዳኢነቱን ያመኑ ገዳማውያ አባቶች በጸሎታቸው ይጠሩታል እርሱም ፈጥኖ ይራዳቸዋል፡፡ እኛም ገዳማውያንን ስንደግፍ፣ በዓታቸውን ስናጸና፣ የበረከታቸው ተሳታፊ እንሆናለን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

ለበለጠ መረጃ:- 09 38 64 44 44/0918077957


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2