በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ ምግብ መሸጫ ውስጥ በመመገብ ላይ የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተደብድበው መገደላቸው ተነገረ። ትናንት ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም በተፈጸመው በዚህ ጥቃት፣ ከኢትዮጵያውያኑ በተጨማሪ ሁለት ናይጄሪያውያን ጭምር ህይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል።
ጥቃቱ የተፈጸመው ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያስመዘገበችበትን የ”ነፃነት ቀን” (Freedom Day) እያከበረች ባለችበት ወቅት ነው። ድርጊቱ መጤ ጠል አራማጅ የሆኑ የሀገሪቱ ዜጎች በስደተኞች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ጥሪ እያደረጉ ባሉበት ወቅት መከሰቱ በስደተኞች ዘንድ ስጋትን ፈጥሯል።
የአካባቢው ፖሊስ ግድያውን አስመልክቶ ምርመራ መጀመሩን ገልጿል። ይሁን እንጂ ስሙ ያልተጠቀሰ አንድ የፖሊስ መኮንን፣ ግድያው “በኢትዮጵያውያኑ መካከል ባለ አለመግባባት የተፈጸመ ሳይሆን አይቀርም” የሚል ጥርጣሬውን ለሚዲያዎች አጋርቷል። የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት በበኩላቸው በድርጊቱ ማዘናቸውን ገልጸው፣ ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እየጠየቁ ይገኛሉ።
DW Amharic
Source: Yeneta Tube









No comments yet.