ኢራን የመከላከያ ቴክኖሎጂዋን ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸች ኢራን ያሏትን የመከላከያ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ኢራን የመከላከያ ቴክኖሎጂዋን ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን ገለጸች
ኢራን ያሏትን የመከላከያ ትጥቅና የቴክኖሎጂ አቅሞች ለ‹‹ገለልተኛ ሀገራት›› በተለይም ደግሞ ለሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራት ለማካፈል ዝግጁ መሆኗን አስታወቀች።
የኢራን ምክትል የመከላከያ ሚኒስትር ሬዛ ታላይ-ኒክ እንደገለጹት፤ ቴህራን በራሷ አቅም ያበለጸገቻቸውን የመከላከያ ትጥቆችና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለወዳጅ ሀገራት ለማጋራት ፍላጎት አላት።
ምክትል ሚኒስትሩ በተለይ ትኩረት የሰጡት የሻንጋይ የትብብር ድርጅት አባል ሀገራትን ሲሆን፤ ኢራን ከእነዚህ ሀገራት ጋር ያላትን ወታደራዊና የመከላከያ ትብብር ለማጠናከር እንደምትፈልግ ጠቁመዋል።
ይህም ለቀጣናው ሰላምና ደህንነት መከበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።
ኢራን በቅርብ ዓመታት በተለይም በሚሳዔል እና በሰው አልባ አውሮፕላኖች (ድሮን) ቴክኖሎጂ ከፍተኛ እድገት ማሳየቷ የሚታወስ ሲሆን፤ ይህ የቴክኖሎጂ ሽግግር ጥሪ የቀረበው ሀገሪቱ በምዕራባውያን አገራት ላይ ያላትን ጥገኝነት ለመቀነስና ከምስራቁ ዓለም ጋር ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በምታደርገው ጥረት አካል እንደሆነ ተነግሯል።
የሻንጋይ የትብብር ድርጅት እንደ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ህንድ እና ፓኪስታን ያሉ ሀገራትን በአባልነት የያዘ ሲሆን ኢራንም በቅርቡ የድርጅቱ ሙሉ አባል መሆኗ ይታወቃል ሲል አል-አረቢያ ዘግቧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: