ከግማሽ ክፍለ ዘመን በኋላ ኤምሬትስ ከኦፔክ ጋር ያላትን አባልነት ማቋረጧ ተሰማ

- Advertisement -
Sidebar AD

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ (UAE) ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ አባል ሆና የቆየችበትን የነዳጅ ላኪ አገራት ድርጅት (ኦፔክ) በይፋ መውጣቷን አስታወቀች።

ይህ በታሪክ አጋጣሚ ከፍተኛ ተጽዕኖ ይኖረዋል ተብሎ የሚታሰበው ውሳኔ፣ በባህረ ሰላጤው አካባቢ ከኢራን ጋር ያለው ወታደራዊ ውጥረት በጨመረበትና የነዳጅ ዋጋ ዳግም ማሻቀብ በጀመረበት ወቅት መምጣቱ ዓለም አቀፉን የኢነርጂ ገበያ ክፉኛ አስደንግጧል።

እ.ኤ.አ. በ1971 ድርጅቱን የተቀላቀለችውና ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ቁልፍ ተዋናይ የነበረችው ኤምሬትስ፣ ከኦፔክ ለመውጣት የወሰነችው የነዳጅ የማምረት አቅሟን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ካላት ፍላጎት ጋር ተያይዞ እንደሆነ ተገምቷል።

ከሳውዲ አረቢያ እና ከኢራቅ በመቀጠል በድርጅቱ ውስጥ ሦስተኛዋ ግዙፍ ነዳጅ አምራች የሆነችው ኤምሬትስ፣ ከአውፔክ መውጣቷ እስካሁን ሲደረግባት የነበረውን የምርት ገደብ እንድታስወግድ በር ይከፍትላታል።

የአገሪቱ ብሔራዊ የዜና አገልግሎት ባወጣው መግለጫ፣ “ኤምሬትስ ከአውፔክ ብትወጣም፣ በዓለም ገበያ ላይ ተጨማሪ ምርት በኃላፊነትና በደረጃ፣ ከገበያው ፍላጎት ጋር በተጣጣመ መልኩ ለማቅረብ ትሰራለች” ብሏል። ይሁን እንጂ ስልታዊ ጠቀሜታ ያለው የሆርሙዝ ሰርጥ በመዘጋቱ ምክንያት፣ የታሰበውን የጨመረ ምርት በፍጥነት ወደ ዓለም ገበያ ለማድረስ ቴክኒካዊ ፈተናዎች ሊገጥሟት እንደሚችሉ የዘርፉ ተንታኞች ስጋታቸውን ገልጸዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአውፔክ መውጣት ድርጅቱ በዓለም የነዳጅ ዋጋ ላይ ያለውን የመወሰን አቅም ሊያዳክመው እንደሚችል ይገመታል። በሌላ በኩል፣ ኤምሬትስ የራሷን ብሔራዊ የኢኮኖሚ ጥቅም ለማስጠበቅና የምርት አቅሟን በነፃነት ለመጠቀም የወሰደችው እርምጃ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ካለው የፖለቲካ ትኩሳት ጋር ተዳምሮ የዓለም ኢኮኖሚን በቀጣይ ወራት ሊፈታተነው እንደሚችል ይጠበቃል።

Via capital


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: