የጤና ተቋማት የ24 ሰዓት አገልግሎት ስለመስጠታቸው ድንገተኛ ቁጥጥር ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የጤና ተቋማት የ24 ሰዓት አገልግሎት መስጠታቸውን ለማረጋገጥ ድንገተኛ ቁጥጥር እንደሚደረግ ያስታወቀው የአዲስ አበባ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ነው።

ባለስልጣኑ በተለይም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተገልጋዮች በሚስተናገዱባቸው ተቋማት ላይ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና ተደራሽነቱን ለማስፋት በትኩረት እየሰራ እንደሆነ ገልጿል።

በባለስልጣኑ የጤና ተቋማት ብቃት ማረጋገጥ ቡድን መሪ ሊሊ ገብረእግዚአብሔር፤ ‹‹ድንገተኛ ክትትሉ በዋናነት ባለሙያዎች በሥራ ገበታቸው ላይ መገኘታቸውንና ለሕክምናው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች መሟላታቸውን ለማረጋገጥ የታለመ ነው›› ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ክትትሉ ምሽትን ጨምሮ በማንኛውም ሰዓት እንደሚካሄድ ገልተዋል፡፡ የቁጥር ስራው ይህም ታካሚዎች ተገቢውን አገልግሎት እንዲያገኙ ለማድረግ ያግዛል ተብሏል።

በከተማዋ ውስጥ አገልግሎት የሚሰጡ ጤና ጣቢያዎችን ጨምሮ በተለያዩ የጤና ተቋማት የሚሰጠው ሕክምና ደህንነቱ የተረጋገጠና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን መጠነ ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙም ቡድን መሪዋ አብራርተዋል።

በእሌኒ ግዛቸው


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: