ድምፃዊ ፀጋአብ አዲሱን አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪያን ሊያበረክት ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | እምበይተይ በተሰኘው ዘፈኑ በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ፀጋአብ ከ15 ዓመታት ቆይታ በኋላ አራተኛ አልበሙን ይዞ ተመልሷል።

ድምፃዊው ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው ዳግማዊ ንጉስ የሚል መጠሪያ የተሰጠው ይህ አዲስ አልበም 12 የተለያዩ ስራዎችን በውስጡ አካቷል።

አጠቃላይ ይዘቱ በፍቅር ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የትግራይን ህዝብ ጽናት ባህል እና እሴቶች የሚያንፀባርቁ ዜማዎች የተካተቱበት እንደሆነም ተገልጿል።

በርካታ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ይህ አልበም በድምፃዊው ናዶና በተሰኘ የዩቲዩብ ቻናል ለታዳሚ እንደሚሰራጭ ታውቋል።

የአልበሙ ዝግጅት በኤርሚ ኤቨንትስ እና በዳይናሚክ ኢንተርቴይመንት ትብብር የተከናወነ ሲሆን ለሙዚቃ አድናቂዎች ልዩ የጥበብ ስራ ይዞ እንደሚቀርብም ተመልክቷል።

የአልበሙ ታላቅ የምረቃ ስነ ስርዓት የፊታችን ሐሙስ ሚያዝያ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል ታዋቂ ግለሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ይከናወናል።

#music #culture #art #ethiopianmusic #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2