ያሬድ ባዬ እና መለሠ ማሩ የወንጀል ድርጊቱን የፈጸሙት ሚያዚያ 16 ቀን 2018 ዓ/ም ከቀኑ 7 ሰዓት 30 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።
ተጠርጣሪዎቹ ተገቢውን የጉምሩክ ሂደት ሳያልፉ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 5 መቶ 41 ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ሌላ ዕቃ በማስመሠል በካርቶን ተሸክመው እየተንቀሳቀሱ ሳለ በአካባቢው በስራ ላይ የነበሩ የፖሊስ አባላት በመጠራጠር ባደረጉት ፍተሻ ከነ ኤግዚቢቶቹ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።
ህጋዊ አግባብነት የጎደላቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች የሀገርን ምጣኔ ሀብት ከመጉዳት ባለፈ በህጋዊ ነጋዴዎችና በንግድ ስርዓቱ ላይ የሚፈጥሩት ጫና ከፍተኛ እንደሆነ በመገንዘብ ሁሉም ዜጋ መሠል ድርጊቶችን ማውገዝ እንደሚገባው የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ጥሪውን አስተላልፏል።
Addis Ababa police


Source: Yeneta Tube









No comments yet.