በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ሶስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ​በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ አንድ የፈጣን ምግብ መሸጫ ውስጥ ባጋጠመ የጥይት ጥቃት፣ ሶስት ኢትዮጵያውያን እና ሁለት ናይጄሪያውያን መገደላቸውን የአገሪቱ ፖሊስ እና የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት አስታወቁ።

ጥቃቱ የተፈጸመው ትናንት፣ ደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ያደረገችበትን እና የነፃነት ቀኗን (Freedom Day) በምታከብርበት ሚያዝያ 27 ቀን ነው።

ኢትዮጵያውያኑ ግድያው የደረሰባቸው በጆሃንስበርግ ከተማ በሚገኝ “ማክዶናልድ” የፈጣን ምግቦች መሸጫ ውስጥ ምግብ በመመገብ ላይ ሳሉ መሆኑ ተገልጿል።

ጥቃቱ የተፈጸመበት ወቅት መጤ ጠል አራማጅ ደቡብ አፍሪካውያን በስደተኞች ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጥሪ እያስተላለፉ ባሉበት ወቅት መሆኑ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ይሁን እንጂ አንድ የአገሪቱ ፖሊስ መኮንን ለተለያዩ አካላት በሰጡት መረጃ፣ ግድያው በኢትዮጵያውያኑ መካከል በነበረ መጠቃቃት ወይም አለመግባባት የተነሳ የተፈጸመ ሊሆን እንደሚችል ያላቸውን ጥርጣሬ ገልጸዋል።

​ፖሊስ ስለ ጥቃቱ መንስኤና ስለ አጥቂዎቹ ማንነት ተጨማሪ ምርመራ እያደረገ ይገኛል።

ዘገባው የ DW ነው

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu
​#ደቡብ_አፍሪካ #ጆሃንስበርግ #ኢትዮጵያ #ዜና #SouthAfrica #Johannesburg #Ethiopians #BreakingNews


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1