በ21 ዓመቴ የኩላሊት ኢንፌክሽን በሽታ እንዳለብኝ የታወቀ ሲሆን በ23 ዓመቴ ትዳር ይዤ ህይወትን መኖር በጀመርኩበት ጊዜ በድንገት ሁለቱም ኩላሊቶቼ መስራት አቆሙ።
ላለፉት 15 ዓመታት የገንዘብ አቅም ኖሮኝ ሳይሆን በአንዳንድ ደጋግ ወገኖች ድጋፍ በኩላሊት እጥበት (በዲያሌሲስ) እስከ አሁን በህይወት አለሁ።
በእነዚህ ዓመታት በእጥበት ወቅት ለሞት የሚዳርጉ ሁኔታዎች ብዙ ጊዜ ያጋጠሙኝ የነበር ቢሆንም እግዚአብሔር ግን ደግፎኝ ዛሬ ደርሻለሁ።
በእነዚህ 15 አመታት፣ ለዳያሊስስ የሚያገለግለው ካቴተር ደም ስሩ ሲዘጋ እየተለወጠ መጀመሪያ ላይ አንገቴ ላይ ቀጥሎ ተራ በተራ ሁለት እጆቼ ላይ በመጨረሻ፣ እግሮቼ ላይ ተደርጎ ዲያሌሲሱ ሲሰራልኝ የቆየ ሲሆን ለረዥም ዓመታት ስለተሰራባቸው የደም ስሮቼ ተዘግተው ጥቅም ላይ መዋል ስላልቻሉ በአሁኑ ወቅት ሀኪሞቹ በጉበቴ ላይ ለማስቀመጥ የመጨረሻውን አማራጭ የሰጡኝ እና ይህም ለስድስት ወራት ብቻ ሊያገለግለኝ እንደሚችልና በህይወት ለመቆየት ያለኝ የመጨረሻ አማራጭ የንቅለ ተከላ ስራ ማሰራት እንደሆነ ገልጸውልኛል፡፡
በተጨማሪም ከዚሁ ጋር ተያይዞ የልብ ከባድ ህመምን ጨምሮ ሌሎች የጤና ችግሮች እያጋጠመኝ ይገኛል።
ወደ ውጭ አገር በመሄድ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ቀዶ ጥገና ሕክምና ለማድረግ የሚረዳ የቦርድ የምስክር ወረቀት እና አስፈላጊውን መረጃዎች ሰጥተውኛል፡፡ እንዲሁም ወንድሜ ኩላሊት ሊሰጠኝ ፈቃደኛ ነው፡፡
ነገር ግን ለህክምና እና ተያያዥ ወጪዎች የሚፈለገው ገንዘብ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) ዶላር ስለሆነና አቅም ስለሌለኝ ይህንን GoFundMe በመክፈት እርዳታ ለመጠየቅ ተገድጃለሁ፡፡
ሁላችሁም አነሰ ሳትሉ የምትችሉትን እንድትደግፉኝና በህይወት እንድቆይ እንድትረዱኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ፡፡ ለምታደርጉልኝ በጎነት አመሰግናለሁ፡፡
https://gofund.me/fde9f3f81


Source: FastMereja









No comments yet.