ኃላፊው በተሾሙ በ45 ቀናት ተነሱ።

- Advertisement -
Sidebar AD

የትግራይ የመገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ስራ አስኪያጅ በተሾሙ በ45 ቀናት ውስጥ ከኃላፊነት መነሳታቸው ምንጮች ገለፁ።

ለስራ አስኪያጁ ቅርበት ያላቸው ምንጮች እንደገለፁት የካቲት 30/2018 ዓ/ም የኤጀንሲው ስራ አስኪያጅ ሆኖው የተሸሙት አባዲ ገ/ስላሴ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል።

ሚያዝያ 16/2018 ዓ.ም በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) የተፃፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ሃላፊው በሁለት መስመር ፅሁፍ ከሃላፊነታቸው እንዲነሱ ተደርገዋል።

ሃላፊው በተሾሙ በ45 ቀናት ውስጥ ለምን ከሃላፊነት እንደተነሱ በደብዳቤው በግልፅ ባይቀመጥም ስራ አስኪያጁ ” ወደ ህወሓት በማዳላት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ስራ አደናቅፈዋል ” በሚል ምክንያት እንደሆነ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ምንጮች ጠቁመዋል።

ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ሚያዝያ 13/2018 ዓ.ም ለሚድያ የሰጡት መግለጫ በክልሉ መንግስታዊ ሚድያዎች ተዛብቶ መሰራጨቱ በመግለፅና በመወቀስ Landa Report እና ላዛ ትግርኛ ለተባሉ የግል ሚድያዎች ሚያዝያ 14/2018 ዓ.ም ተጨማሪ ማስተካከያና ማብራርያ መስጠታቸው ይታወሳል።

ቴሌቪዥን ጣብያው የፕሮግራሞች ዳይሬክተር ጋዜጠኛ አፈወርቂ ገ/ሂወት የስራ አስኪያጁ ስራ ደርበው እንዲሰሩ ከፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ደብዳቤ እንደደረሳቸው ሰምተናል።

አባዲ ገ/ስላሴ ከጦርነት በፊት እና በኋላ የትግራይ ቴሌቬዥንን ለረጅም ዓመታት የመሩት ተሻለ በቀለ ተክተው መሾማቸው መዘገባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia




Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2