የቅን ልቦች የወሩ አሸናፊዎች ታወቁ፤ የ10ሺህ ብር የገንዘብ ሽልማት ተበረከተ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I የቅን ልቦች ማህበራዊ ሚዲያ የያዝነውን ወር አሸናፊዎች ቀድሞ ይፋ ካደረገ በኋላ፣ በቅርቡ በተካሄደው የኤምኤምኤ (MMA) ውድድር ላይ ደማቅ አሻራ ላሳረፉ አካላት ልዩ እውቅና እና የገንዘብ ሽልማት ሰጥቷል።

ባለፉት ወራት ወር በገባ በመጀመሪያዎቹ ቀናት አሸናፊዎችን ይፋ የማድረግ ልምድ የነበረው ተቋሙ፣ በዚህ ወር ልዩ ትኩረቱን በስፖርታዊ ጨዋነታቸው የብዙዎችን ቀልብ በሳቡት ስፖርተኞች ላይ አድርጓል። በዚህም መሰረት፣ በውድድሩ ወቅት ባሳዩት እጅግ የሚደነቅ ስነ-ምግባር እና ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የህዝብ ምስጋና የተቸራቸው ቦክሰኞቹ ኤርሚያስ መስፍን እና መስፍን ብሩ የልዩ ሽልማት ተሸላሚ ሆነዋል።

የቅን ልቦች አዘጋጆች እና ቤተሰቦች ለሁለቱም ቦክሰኞች የ100,000 (አንድ መቶ ሺህ) ብር የገንዘብ ስጦታ አበርክተውላቸዋል። ይህ ሽልማት የተሰጠው ስፖርተኞቹ በሰላማዊ ፉክክር እና በመከባበር ረገድ ላሳዩት አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑ ተገልጿል። በተጨማሪም የውድድሩ አዘጋጆች ለነበራቸው ሚና ተገቢው እውቅና የተሰጣቸው ሲሆን፣ የዚህ ወር አሸናፊዎች ቀድሞ መታወቃቸው በማህበራዊ ሚዲያ ተከታታዮች ዘንድ ከፍተኛ መነቃቃትን ፈጥሯል።





Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2