#FastMereja I የፈረስ ስፖርትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ያለመው 3ኛው የጆርካ ካቫሊያ የፈረስ ግልቢያ ውድድር፣ በመጪው ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ። ጆርካ ኢቨንትስ ከጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጁት በዚህ ውድድር ላይ ስምንት የፈረስ ክለቦች ለከፍተኛ የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት እንደሚፎካከሩ ታውቋል።
የውድድር ቀኑን አስመልክቶ የወጣው ዝርዝር መረጃ እንደሚጠቁመው፣ መርሃ ግብሩ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን፣ ከውድድሩ ባሻገር የጣሊያንና የሀበሻ ምግቦች፣ የሙዚቃ ዝግጅቶች እና የህጻናት መጫወቻዎች ተካተዋል።
ለዝግጅቱ መታደሚያ የሚሆኑ ትኬቶች ከዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌ ብር መተግበሪያ ላይ ለሽያጭ ቀርበዋል። የትኬት ዋጋም፦
ቀድመው ለሚገዙ : ለአዋቂ 2,000 ብር፣ ለህጻናት 1,600 ብር (ምሳን ጨምሮ)።
በዕለቱ ለሚገዙ: ለአዋቂ 2,200 ብር፣ ለህጻናት 1,800 ብር (ምሳን ጨምሮ) መሆኑ ተገልጿል።



Source: FastMereja









No comments yet.