3ኛው የጆርካ ካቫሊያ የፈረስ ግልቢያ ውድድር በታላቅ ድምቀት ሊካሄድ ነው

- Advertisement -
Sidebar AD

​#FastMereja I ​የፈረስ ስፖርትን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ያለመው 3ኛው የጆርካ ካቫሊያ የፈረስ ግልቢያ ውድድር፣ በመጪው ግንቦት 2 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ። ጆርካ ኢቨንትስ ከጣሊያን ኤምባሲ ጋር በመተባበር በሚያዘጋጁት በዚህ ውድድር ላይ ስምንት የፈረስ ክለቦች ለከፍተኛ የገንዘብና የዋንጫ ሽልማት እንደሚፎካከሩ ታውቋል።

​የውድድር ቀኑን አስመልክቶ የወጣው ዝርዝር መረጃ እንደሚጠቁመው፣ መርሃ ግብሩ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ ምሽቱ 11፡00 ሰዓት የሚቆይ ሲሆን፣ ከውድድሩ ባሻገር የጣሊያንና የሀበሻ ምግቦች፣ የሙዚቃ ዝግጅቶች እና የህጻናት መጫወቻዎች ተካተዋል።

​ለዝግጅቱ መታደሚያ የሚሆኑ ትኬቶች ከዛሬ ሚያዝያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በቴሌ ብር መተግበሪያ ላይ ለሽያጭ ቀርበዋል። የትኬት ዋጋም፦

​ቀድመው ለሚገዙ : ለአዋቂ 2,000 ብር፣ ለህጻናት 1,600 ብር (ምሳን ጨምሮ)።

​በዕለቱ ለሚገዙ: ለአዋቂ 2,200 ብር፣ ለህጻናት 1,800 ብር (ምሳን ጨምሮ) መሆኑ ተገልጿል።






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: