“በኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን በጣም በቅርቡ እናነሳለን” – የአውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት በኢራን ላይ የጣለውን ማዕቀብ…

- Advertisement -
Sidebar AD
“በኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን በጣም በቅርቡ እናነሳለን” – የአውሮፓ ህብረት

የአውሮፓ ህብረት በኢራን ላይ የጣለውን ማዕቀብ ለማንሳት ማሰቡን ገልጿል። የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን “እስላማዊ ዘብ ሆርሙዝን ለመክፈት ቢስማማም ባይስማማም፣ ማዕቀቦችን በፍጥነት ለማንሳት እያሰብን ነው” ብለዋል።
ቮንደርሊን “በኢራን ላይ የተጣሉ ማዕቀቦችን በጣም በቅርቡ እናነሳለን” ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቷ “የኢራን መንግስት የእኛን ቁርጠኝነት አይቶ በዜጎች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ማስቆም ይኖርበታል” በማለት ቅድመ ሁኔታ አስቀምጠዋል።
“ማዕቀቡን ከማንሳታችን በፊት ለውጥ ማየት አለብን፣ በህዝባቸው ላይ የሚፈፅሙት በደል እንጂ ማንም በኢራን ላይ ማዕቀብ የመጣል ፍላጐት የለውም” ብለዋል።
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ በቅርቡ ከፈረንሳይ፣ ጀርመን እና ብሪታንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ባደረጉት ውይይት የአውሮፓ ህብረት የጣለውን ማዕቀብ እንዲያነሳ መጠየቃቸው ይታወሳል። 
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1