#Ethiopia | ታሪካዊው ተፈሪ መኮንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ “ዘመን ተሻጋሪ ቅርስ ለቀጣዩ ትውልድ” በሚል መሪ ቃል ላለፉት ወራት ሲያከብረው የቆየውን የ100ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ በደመቀ ስነ-ስርዓት አጠናቋል።
የበዓሉ መዝጊያ መርሃ ግብር የተጀመረው ከኮሌጁ ዋና ህንፃ በመነሳት የካቲት 12 አደባባይን እና ስድስት ኪሎ ዩኒቨርሲቲን በመዞረ ደማቅ የማርሽ ባንድ የታጀበ የክብር ጉዞ ነበር።
የዕለቱ የክብር እንግዳ የነበሩት ወ/ሮ ዳግማዊት ግርማ በስራና ክህሎት ቢሮ በቢሮ ሀላፊ ማእረግ የውጤት ተኮርና ተቋማት ልማት ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሀላፊ እና አቶ ሚደክሳ ከበደ በቢሮ ሀላፊ ደረጃ የኢንተርፕራይዝና ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ሀላፊ የ16ኛውን የቴክኒክና ሙያ ሳምንት አውደ ርዕይ በይፋ የከፈቱት።
የኮሌጁ ዋና ዲን አቶ ተሾመ ፈይሳ ተፈሪ መኮንን ባለፉት መቶ ዓመታት ለሀገር ግንባታ ያበረከተውን አስተዋጽኦና ያለፈበትን ረጅም ጉዞ የሚገልጽ አጭር ሪፖርት አቅርበዋል።
አቶ ሚደክሳ ከበደ በመክፈቻ ንግግራቸው፣ ኮሌጁ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ታሪክ ውስጥ ያለውን ጉልህ ስፍራ አድንቀው፣ ተቋሙ አሁንም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል።
በመርሃ ግብሩ ላይ በኮሌጁ ውስጥ ለ20 ዓመትና ከዚያ በላይ በታማኝነት ላገለገሉ ሰራተኞች፣ የቀድሞ የኮሌጁ ዲኖች እና ተቋሙ ከእንጦጦ ፖሊ ቴክኒክ ወደ ቀድሞ ስያሜው “ተፈሪ መኮንን” እንዲመለስ ጉልህ ሚና ለተጫወቱ አካላት የክብር እውቅና ተሰጥቷል።
Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.